1 ነገሥት 14:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)26 በቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥት ተከማችቶ የነበረውንም ሀብት ሁሉ፥ ሰሎሞን ከወርቅ ያሠራቸውን ጋሻዎች ጭምር ዘርፎ ወሰደ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም26 የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ንብረትና የቤተ መንግሥቱን ንብረት ዘርፎ ወሰደ፤ ሰሎሞን ያሠራው የወርቅ ጋሻ፤ ሰሎሞን ያሠራቸው የወርቅ ጋሻዎች ሁሉ እንኳ ሳይቀሩ ሁሉንም ነገር አጋዘ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም26 በቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥት ተከማችቶ የነበረውንም ሀብት ሁሉ፥ ሰሎሞን ከወርቅ ያሠራቸውን ጋሻዎች ጭምር ዘርፎ ወሰደ፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)26 የእግዚአብሔርን ቤተ መዛግብትና የንጉሡን ቤተ መዛግብት ሁሉ ወሰደ፤ ዳዊትም ከሱባ ንጉሥ ከአድርዓዛር ልጆች እጅ ወስዶ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጣቸውን የወርቅ ጦሮችና ሰሎሞን የሠራቸውን የወርቁን ጋሻና ጦር ሁሉ ወደ ግብፅ ወሰደ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)26 የእግዚአብሔርም ቤተ መዛግብትንና የንጉሥ ቤተ መዛግብትን ወሰደ፤ ሁሉንም ወሰደ፤ ሰሎሞንም የሠራውን የወርቁን ጋሻ ሁሉ ወሰደ። ምዕራፉን ተመልከት |