1 ነገሥት 13:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)29 ነቢዩም ሬሳውን አንሥቶ በአህያው ላይ ጫነው፤ እንዲለቀስለትና እንዲቀበር ወደ ቤትኤል መልሶ ወሰደው፤ ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም29 ስለዚህ፣ ነቢዩ የዚያን የእግዚአብሔር ሰው ሬሳ አንሥቶ በአህያው ላይ ጫነ፤ አልቅሶ ለመቅበርም ራሱ ወደሚኖርበት ከተማ አመጣው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም29 ሽማግሌው ነቢይ ሬሳውን አንሥቶ በአህያው ላይ ጫነው፤ እንዲለቀስለትና እንዲቀበር ወደ ቤትኤል መልሶ ወሰደው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)29 ነቢዩም የእግዚአብሔርን ሰው ሬሳ አነሣ፤ በአህያውም ላይ ጫነው፤ ነቢዩም በራሱ መቃብር ይቀብረው ዘንድ ወደ ገዛ ከተማው አመጣው፤ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)29 ነቢዩም የእግዚአብሔርን ሰው ሬሳ አነሣ፤ በአህያውም ላይ ጭኖ መለሰው፤ ያለቅስለትና ይቀብረው ዘንድ ወደ ገዛ ከተማው ይዞት መጣ። ምዕራፉን ተመልከት |