Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ነገሥት 1:37 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 ንጉሥ ሆይ! ጌታ ከአንተ ጋር እንደሆነ ሁሉ ከሰሎሞንም ጋር ይሁን፤ መንግሥቱንም በዘመንህ ከነበረው የበለጠ ታላቅ ያድርገው!” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 እግዚአብሔር ከጌታዬ ከንጉሡ ጋራ እንደ ነበረ ሁሉ፣ ከሰሎሞንም ጋራ ይሁን፤ ዙፋኑንም ከጌታዬ ከንጉሥ ዳዊት ዙፋን የበለጠ ያድርገው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 ንጉሥ ሆይ! እግዚአብሔር ከአንተ ጋር እንደ ሆነ ሁሉ ከሰሎሞንም ጋር ይሁን፤ መንግሥቱንም በዘመንህ ከነበረው የበለጠ ታላቅ ያድርገው!” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጌ​ታዬ ከን​ጉሥ ጋር እንደ ነበረ እን​ዲሁ ከሰ​ሎ​ሞን ጋር ይሁን፤ ዙፋ​ኑ​ንም ከጌ​ታዬ ከን​ጉሡ ከዳ​ዊት ዙፋን የበ​ለጠ ያድ​ርግ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 እግዚአብሔር ከጌታዬ ከንጉሥ ጋር እንደ ነበረ እንዲሁ ከሰሎሞን ጋር ይሁን! ዙፋኑንም ከጌታዬ ከንጉሡ ዳዊት ዙፋን የበለጠ ያድርግ!”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ነገሥት 1:37
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኢዮአብ ግን ንጉሡን፥ “ጌታ አምላክህ ሕዝቡን መቶ ዕጥፍ ያድርገው፤ የጌታዬ የንጉሡ ዐይን ይህን ለማየት ያብቃው፤ ንጉሡ ጌታዬ ግን ይህን ለማድረግ የፈለገው ለምንድን ነው?” ሲል መለሰለት።


የዮዳሄም ልጅ በናያስ መልሶ ለንጉሡ አለ፦ “ያበጅ ያድርግ፥ የጌታዬም የንጉሥ ጌታ ይህን ይናገር።


የንጉሡም ባርያዎች ገብተው፦ ‘እግዚአብሔር የሰሎሞንን ስም ከስምህ ዙፋኑንም ከዙፋንህ የበለጠ ያድርግ!’ ብለው ጌታችንን ንጉሡን ዳዊትን ባረኩ፥ ንጉሡም በአልጋው ላይ ሆኖ ሰገደ።


በዚያም ኤልያስ ኤልሳዕን “እኔ ከአንተ ከመወሰዴ በፊት ምን እንዳደርግልህ እንደምትፈልግ ንገረኝ” አለው። ኤልሳዕም “የአንተ ተተኪ እንድሆን የሚያስችል መንፈስ በእጥፍ ስጠኝ” ሲል መለሰለት።


ዳዊትም ልጁን ሰሎሞንን እንዲህ አለው፦ “ጠንክር፥ አይዞህ፥ አድርገውም፤ አምላኬ እግዚአብሔር አምላክ ከአንተ ጋር ነውና አትፍራ፥ አትደንግጥም፥ ለእግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት የሚሆነው ሥራ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ እርሱ አይተውህም፥ አይጥልህምም።


ጌታም ሰሎሞንን በእስራኤል ሁሉ ፊት እጅግ አገነነው፤ ከእርሱ በፊትም ለነበሩት ለእስራኤል ነገሥታት ያልሆነውን የመንግሥት ክብር ሰጠው።


የዳዊት ልጅ ሰሎሞንም በመንግሥቱ ላይ ራሱን አጸና፤ ጌታ አምላኩም ከእርሱ ጋር ነበረ፥ እጅግም አገነነው።


ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደሆንሁ እወቁ፥ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።


አሕዛብ ተናወጡ መንግሥታትም ተረበሹ፥ እርሱ ቃሉን ሰጠ፥ ምድርም ተንቀጠቀጠች።


ከባሕር እስከ ባሕር ድረስ፥ ከወንዝም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይግዛ።


እርሱ፦ አባቴ አንተ ነህ፥ አምላኬ የመድኃኒቴም መጠጊያ ይላል።


እርሱም፦ “እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እኔም እንደ ላክሁህ ምልክትህ ይህ ይሆናል፤ ሕዝቡን ከግብጽ ባወጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ እግዚአብሔርን ታገለግላላችሁ” አለ።


ተመካከሩ፤ ግን አይሳካም፤ ዕቅድ አውጡ፤ ሆኖም አይጸናም፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነውና።


“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል፤” ትርጉሙም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፤” ማለት ነው።


እንግዲህ ስለ እነዚህ ነገሮች ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?


በሁሉም ነገር ለሙሴ እንደ ታዘዝን እንዲሁ ለአንተ ደግሞ እንታዘዛለን፤ ብቻ ጌታ አምላክህ ከሙሴ ጋር እንደ ነበረ ከአንተ ጋር ይሁን።


በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ማንም አይቋቋምህም፤ ከሙሴ ጋር እንደ ነበርሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ አልጥልህም፥ አልተውህምም።


ነገር ግን አባቴ ክፉ አስቦብህ፥ ይህን ሳላሳውቅህ ብቀርና በሰላም እንድትሄድ ባላደርግ፥ ጌታ ክፉ ያድርግብኝ፤ ከዚያም የባሰ ያምጣብኝ። ጌታ ከአባቴ ጋር እንደ ነበር እንደዚሁ ከአንተም ጋር ይሁን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች