Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ዜና መዋዕል 9:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 የቆሬም ልጅ የአብያሳፍ ልጅ የቆሬ ልጅ ሰሎም ከአባቱም ቤት የነበሩ ወንድሞቹ ቆሬያውያን በማገልገል ሥራ ላይ ነበሩ፥ አባቶቻቸውም የጌታን ሰፈር መግቢያ ይጠብቁ እንደ ነበር እንዲሁ የድንኳኑን የመግቢያ ደጅ ይጠብቁ ነበር።።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 የቆሬ ልጅ የአብያሳፍ ልጅ፣ የቆሬ ልጅ ሰሎምና ከርሱም ቤተ ሰብ የሆኑት ቆሬያውያን ወደ እግዚአብሔር ማደሪያ የሚያስገባውን በር ይጠብቁ እንደ ነበር ሁሉ፣ እነዚህም ወደ ቤተ መቅደሱ የሚያስገባውን በር ይጠብቁ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 የኤቢያሳፍ የልጅ ልጅ የቆሬ ልጅ ሻሉም የቆሬ ጐሣ አባሎች ከሆኑት ከሌሎች ዘመዶቹ ጋር በመሆን የቀድሞ አባቶቻቸው የእግዚአብሔርን ሰፈር ይጠብቁ በነበረው ዐይነት እግዚአብሔር ወደሚመለክበት ድንኳን የሚያስገባውን በር ይጠብቁ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 የቆ​ሬም ልጅ የአ​ብ​ያ​ሳፍ ልጅ የቆሬ ልጅ ሰሎም ከአ​ባቱ ቤት የነ​በሩ ወን​ድ​ሞቹ ቆሬ​ያ​ው​ያን በማ​ገ​ል​ገል ሥራ ላይ ነበሩ፤ የድ​ን​ኳ​ኑ​ንም መድ​ረክ ይጠ​ብቁ ነበር። አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሰፈር መግ​ቢያ ይጠ​ብቁ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 የቆሬም ልጅ የአብያሳፍ ልጅ የቆሬ ልጅ ሰሎም ከአባቱም ቤት የነበሩ ወንድሞቹ ቆሬያውያን በማገልገል ሥራ ላይ ነበሩ፤ የድንኳንኑም መድረክ ይጠብቁ ነበር። አባቶቻቸውም የእግዚአብሔርን ሰፈር መግቢያ ጠብቀው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ዜና መዋዕል 9:19
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዮዳሄ በበኩሉ ዐታልያ በቤተ መቅደሱ ክልል ውስጥ እንድትገደል አልፈለገም፤ ስለዚህም የጦር አለቆቹን “ግራና ቀኝ በተሰለፉት ዘቦች መካከል አውጥታችሁ ውሰዱአት፤ እርሷን ለመከተል የሚሞክር ቢኖር ይገደል” ሲል አዘዛቸው።


የጦር መኰንኖቹም ዮዳሄ የሰጠውን መመሪያ በመቀበል በሰንበት ቀን ለዘብ ጥበቃ የሚሰማሩትንና ከዘብ ጥበቃም የሚወጡትን ጭፍሮቻቸውን ጭምር አሰልፈው ወደ እርሱ አመጡ።


ሣጥኑም በሚሞላበት ጊዜ የቤተ መንግሥቱ ጸሐፊና ሊቀ ካህናቱ እየመጡ ብሩን በመቁጠር በከረጢት እያሰሩ ያኖሩት ነበር።


እስከ ዛሬም ድረስ በንጉሥ በር በምሥራቅ በኩል ሰፍረዋል፤ ለሌዊ ልጆች ሰፈር በርም ጠባቂዎች ነበሩ።


አስቀድሞም የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ አለቃቸው ነበረ፤ ጌታም ከእርሱ ጋር ነበረ።


ለመዘምራን አለቃ፥ የቆሬ ልጆች ትምህርት።


ለመዘምራን አለቃ፥ የቆሬ ልጆች ትምህርት።


ለመዘምራን አለቃ፥ የቆሬ ልጆች መዝሙር።


አቤቱ፥ መታመናችንን እይልን፥ ወደ ቀባኸውም ፊት ተመልከት።


ወደ ጌታም ቤት የደጁ ጠባቂ በሆነው በሰሎም ልጅ በመዕሤያ ጓዳ በላይ ባለው በአለቆች ጓዳ አጠገብ ወደሚገኘው፥ ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ጌዴልያ ልጅ ወደ ሐናን ልጆች ጓዳ አስገባኋቸው።


የዘበኞቹም አለቃ ታላቁን ካህን ሠራያን በማዕረጉም ሁለተኛ የነበረውን ካህን ሶፎንያስን የደጃፉም ጠባቂዎች የነበሩትን ሦስቱን ሰዎች ወሰደ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች