1 ዜና መዋዕል 6:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)32 እነርሱም ሰሎሞን የጌታን ቤት በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ በመገናኛ ድንኳን ማደሪያ ፊት እያዜሙ ያገለግሉ ነበር፤ በየተራቸውም ያገለግሉ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም32 እነርሱም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ፣ በማደሪያው፣ ይኸውም በመገናኛው ድንኳን ፊት ሆነው እየዘመሩ ያገለግሉ ነበር፤ አገልግሎታቸውንም የሚያከናውኑት በወጣላቸው ደንብ መሠረት ነው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም32 ንጉሥ ሰሎሞን በኢየሩሳሌም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ከመሥራቱ በፊት እግዚአብሔር በሚመለክበት ድንኳን የመዘመር ተግባራቸውን ያከናውኑ ነበር፤ የሥራቸውንም ቅደም ተከተል በተዘጋጀላቸው ተራ መሠረት ይፈጽሙ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)32 ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤት በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ በምስክሩ ድንኳን ማደሪያ ፊት በበገና እያዜሙ ያገለግሉ ነበር፤ በየተራቸውም ለአገልግሎታቸው ይቆሙ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)32 ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤት በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ በመገናኛ ድንኳን ማደሪያ ፊት እያዜሙ ያገለግሉ ነበር፤ በየተራቸውም ያገለግሉ ነበር። ምዕራፉን ተመልከት |