Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ዜና መዋዕል 23:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ዳዊትም በሸመገለ ጊዜ፥ ዕድሜንም በጠገበ ጊዜ ሰሎሞንን በእስራኤል ላይ አነገሠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ዳዊት በሸመገለና ዕድሜው በገፋ ጊዜ፣ ልጁን ሰሎሞንን በእስራኤል ላይ አነገሠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ዳዊት በጣም በሸመገለ ጊዜ ልጁን ሰሎሞንን በእስራኤል ላይ አነገሠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ዳዊ​ትም በሸ​መ​ገለ ጊዜ፥ ዕድ​ሜ​ንም በጠ​ገበ ጊዜ ልጁን ሰሎ​ሞ​ንን በእ​ርሱ ፋንታ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አነ​ገ​ሠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ዳዊትም በሸመገለ ጊዜ፥ ዕድሜንም በጠገበ ጊዜ ሰሎሞንን በእስራኤል ላይ አነገሠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ዜና መዋዕል 23:1
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በመጨረሻዋ እስትንፋሱ አብርሃም ነፍሱን ሰጠ፥ በመልካምም ሽምግልና ሞተ፥ ሸምግሎ፥ ብዙ ዘመንም ጠገበ፥ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ።


ይስሐቅም ነፍሱን ሰጠ፥ ሞተም፥ ሸምግሎ ዕድሜንም ጠግቦ ወደ ወገኖቹ ተከማቸ፥ ልጆቹም ዔሳውና ያዕቆብ ቀበሩት።


ንጉሡ ዳዊትም ዕድሜው ገፍቶ ስለ ሸመገለ፥ ልብስ ደራርበው ቢያለብሱትም ሙቀት ሊሰጠው አልቻለም ነበር።


በውኑ ይህ ነገር ከጌታዬ ከንጉሡ የተደረገ ነውን? ለባርያህም ከአንተ በኋላ በጌታዬ በንጉሡ ዙፋን ላይ የሚቀመጠውን አልነገርህምን?”


በእውነት ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፥ በእኔም ፋንታ በዙፋኔ ላይ ይቀመጣል ብዬ በእስራኤል አምላክ በጌታ እንደ ማልሁልሽ፥ እንዲሁ ዛሬ በእውነት አደርጋለሁ” ብሎ ማለ።


ሰሎሞንም በአባቱ እግር ተተክቶ ነገሠ፤ የመንግሥቱም ሥልጣን እጅግ የጸና ሆነ።


የእስራኤልንም ሹማምንት ሁሉ፥ ካህናቱንም፥ ሌዋውያኑንም ሰበሰበ።


ጌታም ብዙ ልጆች ሰጥቶኛልና ከልጆቼ ሁሉ በጌታ መንግሥት ዙፋን ላይ ተቀምጦ በእስራኤል ላይ እንዲነግሥ ልጄን ሰሎሞንን መርጦታል።


ዕድሜም፥ ባለጠግነትም፥ ክብርም ጠግቦ በመልካም ሽምግልና ሞተ፤ ልጁም ሰሎሞን በእርሱ ፋንታ ነገሠ።


የእህሉ ነዶ ወራቱ ሲደርስ ወደ አውድማ እንደሚገባ፥ ዕድሜ ጠግበህ ወደ መቃብር ትገባለህ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች