1 ዜና መዋዕል 19:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 እነርሱም ወደመጡበት ተመለሱ። ዳዊትም በሰዎቹ ላይ የተደረገውን በነገረሩት ጊዜ ሰዎቹ እጅግ ስላፈሩ እንዲቀበሏቸው መልእክተኞችን ላከ፤ ንጉሡም፦ “ጢማችሁ እስኪያድግ ድረስ በኢያሪኮ ተቀመጡ፥ ከዚያም በኋላ ተመለሱ” አለ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 በሰዎቹ ላይ የደረሰባቸውን ዳዊት በሰማ ጊዜ እጅግ ዐፍረው ስለ ነበር፣ ወደ እነርሱ መልክተኞችን ላከ፤ ንጉሡም፣ “ጢማችሁ እስኪያድግ ድረስ በኢያሪኮ ቈዩና ከዚያ በኋላ ትመጣለችሁ” አለ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 እነርሱም ወደ ቤታቸው ለመመለስ አፈሩ፤ ዳዊት ስለ ሆነው ነገር ሁሉ በሰማ ጊዜ መልእክተኞች ልኮ በኢያሪኮ እንዲቈዩና ጢማቸው እስከሚያድግ ድረስ እንዳይመለሱ ነገራቸው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 ሰዎችም ሄደው በሰዎቹ ላይ የተደረገውን ለዳዊት አስታወቁት። ሰዎቹም በብዙ አፍረዋልና ይቀበሏቸው ዘንድ ሰዎችን ላኩ፤ ንጉሡም፥ “ጢማችሁ እስኪያድግ ድረስ በኢያሪኮ ተቀመጡ፥ ከዚያም በኋላ ተመለሱ” አለ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 ወሬኞችም ሄደው በሰዎቹ ላይ የተደረገውን ለዳዊት አስታወቁት። ሰዎቹም በብዙ አፍረዋልና ተቀባዮች ላከ፤ ንጉሡም “ጢማችሁ እስኪያድግ ድረስ በኢያሪኮ ተቀመጡ፤ ከዚያም በኋላ ተመለሱ፤” አለ። ምዕራፉን ተመልከት |