1 ዜና መዋዕል 18:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ዳዊትም በደማስቆ ሶርያ የጦር ሠራዊት አሰፈረ፤ ሶርያውያንም ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፥ ግብርም አመጡለት። ጌታም ዳዊት በሄደበት ሁሉ ድል አድራጊ አደረገው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ከዚያም በሶርያ ግዛት ውስጥ ባለችው በደማስቆ የጦር ሰፈር አቋቋመ፤ ሶርያውያንም ገባሮቹ ሆኑ፤ ግብርም አመጡለት። እግዚአብሔርም ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ድልን ሰጠው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ከዚያም በኋላ በግዛታቸው ላይ የጦር ሰፈር አቋቋመ፤ ሕዝቡም ግብር እየከፈለ ለእርሱ ተገዛ፤ እግዚአብሔር ዳዊትን በየስፍራው ድል አድራጊ አደረገው፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ዳዊትም በደማስቆ ሶርያ ጭፍሮችን አኖረ፤ ሶርያውያንም ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፤ ግብርም አመጡለት። እግዚአብሔርም ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ያድነው ነበር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ዳዊትም በደማስቆ ሶርያ ጭፍሮች አኖረ፤ ሶርያውያንም ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፤ ግብርም አመጡለት። እግዚአብሔርም ዳዊት በሄደበት ሁሉ ድል ይሰጠው ነበር። ምዕራፉን ተመልከት |