1 ዜና መዋዕል 13:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 የጌታም ቁጣ በዖዛ ላይ ነደደ፥ እጁንም ወደ ታቦቱ ስለዘረጋ ቀሠፈው፤ በዚያም በእግዚአብሔር ፊት ሞተ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 ታቦቱን በእጁ ስለ ነካ፣ የእግዚአብሔር ቍጣ በዖዛ ላይ ነደደ፤ ስለዚህም በዚያው በእግዚአብሔር ፊት ሞተ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 ዑዛ ታቦቱን በመንካቱ እግዚአብሔር ተቈጥቶ ወዲያውኑ በሞት ቀሠፈው፤ ስለዚህም ዑዛ በዚያው በእግዚአብሔር ፊት ሞተ፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 እግዚአብሔርም በዖዛ ላይ ተቈጣ። እጁንም ወደ እግዚአብሔር ታቦት ስለ ዘረጋ ቀሠፈው፤ በዚያም በእግዚአብሔር ፊት ሞተ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 የእግዚአብሔርም ቍጣ በዖዛ ላይ ነደደ፤ እጁንም ወደ ታቦቱ ስለዘረጋ ቀሠፈው፤ በዚያም በእግዚአብሔር ፊት ሞተ። ምዕራፉን ተመልከት |