Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ዜና መዋዕል 12:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 በጽኑ የሠለጠኑ ተዋጊዎች ለውግያም የተዘጋጁ፥ የማያመነቱ፥ ሁሉንም ዓይነት የጦር መሣሪያ የታጠቁ የዛብሎን ሰዎች ኀምሳ ሺህ ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ልምድ ያላቸው፣ በሁሉም ዐይነት መሣሪያ ለመዋጋት የተዘጋጁና ዳዊትን ለመርዳት የመጡት መንታ ልብ የሌላቸው የዛብሎን ሰዎች ኀምሳ ሺሕ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 በጭ​ፍ​ራ​ውም ውስጥ ዳዊ​ትን ለመ​ር​ዳት የወጡ የተ​ዘ​ጋጁ፥ መሣ​ሪ​ያም ሁሉ የያዙ የዛ​ብ​ሎን ሰዎች አምሳ ሺህ ነበሩ፤ ከእ​ነ​ርሱ አን​ድስ እንኳ ደካማ አል​ነ​በ​ረም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 በጭፍራውም ውስጥ የወጡ ለሰልፍም የተዘጋጁ፥ የማያመነቱ፥ መሣሪያም ሁሉ የያዙ የዛብሎን ሰዎች አምሳ ሺህ ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ዜና መዋዕል 12:33
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የንፍታሌምም አለቆች አንድ ሺህ ነበሩ፥ ከእነርሱም ጋር ጋሻና ጦር የታጠቁ ሠላሳ ሰባት ሺህ ነበሩ።


በጽኑ የሠለጠኑ ተዋጊዎች፥ ለውጊያም የተዘጋጁ የአሴር ሰዎች አርባ ሺህ ነበሩ።


እነዚህ ሁሉ ተዋጊዎች በሰልፍ ዳዊትን በእስራኤል ሁሉ ላይ ለማንገሥ በፍጹም ልባቸው ወደ ኬብሮን መጡ፤ ደግሞም ከእስራኤል የቀሩት ሁሉ ዳዊትን ለማንገሥ በአንድ ልብ ነበሩ።


አቤቱ፥ አድነኝ፥ ደግ ሰው አልቆአልና፥ ከሰው ልጆችም መተማመን ጐድሎአልና።


ኢየሱስ ናትናኤልን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ ስለ እርሱ “ተንኰል የሌለበት እውነተኛ የእስራኤል ሰው እነሆ!” አለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች