1 ዜና መዋዕል 10:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 እንዲሁ ሳኦል በጌታ ላይ ስላደረገው ኃጢአት፥ የጌታንም ቃል ስላልጠበቀ ሞተ። ደግሞም መናፍስት ጠሪ ስለ ጠየቀ፥ ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 ሳኦል ለእግዚአብሔር ስላልታመነ ሞተ፤ የእግዚአብሔርን ቃል አልጠበቀም፤ ይልቁንም ከሙታን ጠሪ ምክርን ጠየቀ፤ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13-14 ሳኦል ለእግዚአብሔር ታማኝ ሆኖ ባለመገኘቱ ምክንያት ሞተ፤ እርሱ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ አልፈጸመም፤ እንዲያውም የሙታን መናፍስት ጠሪዎችን በመጠየቅ መመሪያ ለማግኘት ሞከረ እንጂ እግዚአብሔርን አልጠየቀም፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ገደለው፤ መንግሥቱንም ወደ እሴይ ልጅ ወደ ዳዊት አስተላለፈ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 እንዲሁ ሳኦል በእግዚአብሔር ላይ ስላደረገው ኀጢአት፥ እግዚአብሔርም እንዳዘዘው የእግዚአብሔርን ቃል ስላልጠበቀ ሞተ። ደግሞም መናፍስት ጠሪን ጠየቀ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 እንዲሁ ሳኦል በእግዚአብሔር ላይ ስላደረገው ኀጢአት፥ የእግዚአብሔርንም ቃል ስላልጠበቀ ሞተ። ምዕራፉን ተመልከት |