Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማሕልየ መሓልይ 8:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እነሆ፥ እኔ ቅጽር ነኝ፤ ጡቶቼም እንደ ቅጽር ማማዎች ናቸው፤ ከውዴ ጋር ስሆን እርሱ ደስታንና ሰላምን ያገኛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እነሆ እኔ ቅጥር ነኝ፤ ጡቶቼም እንደ ማማ ግንቦች ናቸው፤ እኔም በዐይኖቹ ፊት፣ ሰላምን እንደሚያመጣ ሰው ሆንሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እኔ ቅጥር ነኝ ጡቶቼም እንደ ግንብ ናቸው፥ በዚያን ጊዜ በፊቱ ሰላምን እንደምታገኝ ሆንሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እኔ ቅጥር ነኝ፥ ጡቶ​ችም እንደ ግንብ ናቸው፤ በዚያ ጊዜ በፊቱ ሰላ​ምን እን​ደ​ም​ታ​ገኝ ሆንሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እኔ ቅጥር ነኝ ጡቶቼም እንደ ግንብ ናቸው፥ በዚያን ጊዜ በፊቱ ሰላምን እንደምታገኝ ሆንሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማሕልየ መሓልይ 8:10
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይሁን እንጂ ኖኅ የተባለው ሰው በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስን አግኝቶ ነበር።


ይህን ብታደርግ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት መወደድንና መልካም ዝናን ታገኛለህ።


አንገትሽ በሺህ የሚቈጠሩ የኀያላን ጋሻዎችና የጦር ዕቃዎች ተሰቅለው የሚታዩበትን፥ የጦር ምሽግ ይሆን ዘንድ የተሠራውን የዳዊትን ግንብ ይመስላል።


ሁለቱ ጡቶችሽ መንታ ሆነው የተወለዱና በሱፍ አበባዎች መካከል የተሰማሩ የዋልያ ግልገሎችን ይመስላሉ።


ሰሎሞን በባዓልሃሞን የወይን ተክል ቦታ ነበረው፤ የወይኑንም ተክል ቦታ ለአትክልተኞች አከራየው፤ እያንዳንዳቸውም አንድ ሺህ ብር ያመጡለት ነበር፤


እኔ በቊጣዬ ቀጥቼሽ ነበር፤ አሁን ግን እራራልሻለሁ። ባዕዳን ሕዝቦች ቅጽሮችሽን ይሠራሉ፤ ንጉሦቻቸውም ያገለግሉሻል።


ምቾት እንዳለው ተክል እንድታድጊ አደረግሁ፤ ቁመትና ጠንካራ ሰውነት በመጨመር አድገሽ የተዋብሽ ወጣት ሆንሽ፤ ጡትሽ አጐጠጐጠ፤ ጠጒርሽ ረዘመ፤ ነገር ግን እርቃንሽን ነበርሽ።


መልአኩም እንዲህ አላት፤ “ማርያም ሆይ! በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ አግኝተሻልና አትፍሪ፤


ይህንንም ያደረገው በተወደደው ልጁ አማካይነት በነጻ የሰጠን ክቡር ጸጋ እንዲመሰገን ነው።


ጸጋውንም በጥበብና በዕውቀት ሁሉ አብዝቶ አፈሰሰልን።


ነገር ግን ምሕረት ተደረገልኝ፤ ምሕረት የተደረገልኝም ኢየሱስ ክርስቶስ ወሰን የሌለውን ትዕግሥቱን ከሁሉ የባስሁ ኀጢአተኛ በሆንኩት በእኔ ላይ በማሳየቱ በእርሱ ለሚያምኑና የዘለዓለም ሕይወት ለሚያገኙ ምሳሌ እንድሆን ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች