በመኳንንትም መካከል ትጠቅማለች፤ በአለቆችም መካከል ትታያለች፤ ልዩ ወደ ሆኑ ወደ አሕዛብም ሀገር ትገባለች፤
ልዑላኑን ያገለግላል፥ መሪዎች ባሉበትም አይጠፋም። ወደ ውጭ ሀገሮችም ይጓዛል፥ የሰውን ደግነትና ክፋት ጠንቅቆ ያውቃል።