መዝሙር 7:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ አምላኬ፥ እንዲህስ ካደረግሁ፥ ዐመፃም በእጄ ቢኖር፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ይህን አድርጌ ከሆነ፣ በደልም በእጄ ከተገኘ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነፍሴን እንደ አንበሳ ነጥቀው እንዳይሰብሩዋት፥ የሚያድንና የሚታደግ ሳይኖር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! አንድን ሰው እንኳ በድዬ ከሆነ፥ ለወዳጄ በመልካም ፈንታ ክፉ መልሼ ከሆነ፥ ጠላቴን ያለ ምክንያት እንዲሁ ጐድቼው ከሆነ፥ ከነዚህ ሁሉ ነገሮች አንዱን እንኳ አድርጌ ከሆነ፥ |
“እግዚአብሔር አምላክ ነው፤ ጌታም ነው፤ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ ነው፤ እርሱ ያውቃል። እስራኤልም ያውቀዋል። በእግዚአብሔር ፊት ያደረግነው ለበደልና ለመካድ ከሆነ ዛሬ አያድነን፤
እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ከባሪያህ ጋር አድርገሃልና ለባሪያህ ቸርነትን አድርግ፤ በደል ግን ቢገኝብኝ አንተ ግደለኝ፤ ለምን ወደ አባትህ ታደርሰኛለህ?”
ሳኦልም፥ “አንተ ከእሴይ ልጅ ጋር ለምን ዶለትህብኝ? እንጀራና ሰይፍ ሰጠኸው፤ ዛሬም እንደ ተደረገው ጠላት ሆኖ ይነሣብኝ ዘንድ እግዚአብሔርን ስለ እርሱ ጠየቅህለት” አለው።
ሁላችሁ በላዬ ዶልታችሁ ተነሣችሁብኝ፤ ልጄ ከእሴይ ልጅ ጋር ሲማማል ማንም አልገለጠልኝም፤ ከእናንተም አንድ ለእኔ የሚያዝን የለም፤ ዛሬም እንደ ሆነው ሁሉ ልጄ አገልጋዬን እንዲዶልት ሲያስነሣብኝ ማንም አላስታወቀኝም” አላቸው።
እነሆ፥ ዛሬ በዋሻው ውስጥ እግዚአብሔር በእጄ አሳልፎ እንደ ሰጠህ ዐይንህ አይታለች፤ አንተንም እንድገድልህ ሰዎች ተናገሩኝ፤ እኔ ግን፦ በእግዚአብሔር የተቀባ ነውና እጄን በጌታዬ ላይ አልዘረጋም ብዬ ራራሁልህ።
ከእርሱም በኋላ ዳዊት ደግሞ ተነሣ፤ ከዋሻውም ወጣ፤ ከሳኦልም በኋላ፦“ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ!” ብሎ ጮኸ፤ ሳኦልም ወደ ኋላው ተመለከተ፤ ዳዊትም ወደ ምድር ተጐንብሶ እጅ ነሣ።