እግዚአብሔር የእውነት ዳኛ ነው፤ ኀይለኛም ታጋሽም ነው፤ ሁልጊዜም ጥፋትን አያመጣም።
እግዚአብሔር ጻድቅ ዳኛ ነው፤ ቍጣውንም በየዕለቱ የሚገልጥ አምላክ ነው።
ጋሻዬ በእግዚአብሔር ዘንድ ነው ልበ ቅኖችን የሚያድናቸው።
እግዚአብሔር ሁልጊዜ በክፉዎች ላይ የሚፈርድ ትክክለኛ ዳኛ ነው።
እነሆ፥ እውነትን ወደድህ፤ የማይነገር ስውር ጥበብህን አስታወቅኸኝ።
እግዚአብሔር በሕዝብ ላይ ይፈርዳል፤ አቤቱ አምላኬ፥ እንደ ጽድቅህ ፍረድልኝ፤ እንደ የዋህነቴም ይሁንልኝ።
እግዚአብሔር ቀናተኛና ተበቃይ አምላክ ነው፣ እግዚአብሔር ተበቃይና መዓትን የተሞላ ነው፣ እግዚአብሔር ተቃዋሚዎቹን ይበቀላል፥ ለጠላቶቹም ቍጣውን ይጠብቃል።
በቍጣው ፊት የሚቆም ማን ነው? የቍጣውንም ትኵሳት ማን ይታገሣል? መዓቱ እንደ እሳት ይፈስሳል፥ ከእርሱም የተነሣ ዓለቆች ተሰነጠቁ።