በሞት የሚያስብህ የለምና፥ በሲኦልም የሚያመሰግንህ ማን ነው?
በሞት የሚያስታውስህ የለምና፤ በሲኦልስ ማን ያመሰግንሃል?
አቤቱ፥ ተመለስ ነፍሴንም አድናት፥ ስለ ቸርነትህም አድነኝ።
ከሞቱት መካከል አንድም የሚያስታውስህ የለም። በመቃብርስ ሆኖ የሚያመሰግንህ ማነው?
ሕያው እንድሆን ቃልህንም እንድጠብቅ ለባሪያህ ስጠው።
ተቸግሬአለሁና አቤቱ ይቅር በለኝ፥ ዐይኔም ከቍጣ የተነሣ ታወከች፥ ነፍሴም፥ ሆዴም።
በተኵላና በእባብ ላይ ትጫናለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ።
አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና ዐሳብ፥ ዕውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምትችለውን ሁሉ እንደ ኀይልህ አድርግ።
ነገር ግን ቀን ሳለ የላከኝን ሥራ ልሠራ ይገባኛል፤ ማንም ሥራ ሊሠራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለችና።