ከእርሱም ጋር የእግዚአብሔርን ታቦት የተሸከሙ ሰባት መሰንቆ የሚመቱ ክፍሎች ነበሩ። በሬዎችንና በጎችን ይሠዉ ነበር።
ዘኍል 7:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለቀዓት ልጆች ግን መቅደሱን ማገልገል የእነርሱ ነውና፥ በትከሻቸውም ይሸከሙት ነበርና ምንም አልሰጣቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኀላፊነት የተሰጧቸውን ንዋያተ ቅድሳት በትከሻቸው መሸከም ስለ ነበረባቸው፣ ሙሴ ለቀዓታውያን ምንም አልሰጣቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለቀዓት ልጆች ግን በትከሻቸው በመሸከም ቅዱስ የሆኑትን ነገረሮች ማገልገል የእነርሱ ነበርና፥ ለእነርሱ ምንም አልሰጣቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእነርሱ ኀላፊነት የሚጠበቁት ንዋያተ ቅድሳት በትከሻቸው የሚሸከሙአቸው ስለ ሆኑ ሙሴ ለቀዓታውያን ሠረገሎችንም ሆነ በሬዎችን አልሰጣቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለቀዓት ልጆች ግን መቅደሱን ማገልገል የእነርሱ ነውና፥ በትከሻቸውም ይሸከሙት ነበርና ምንም አልሰጣቸውም። |
ከእርሱም ጋር የእግዚአብሔርን ታቦት የተሸከሙ ሰባት መሰንቆ የሚመቱ ክፍሎች ነበሩ። በሬዎችንና በጎችን ይሠዉ ነበር።
የእግዚአብሔርንም ታቦት በአዲስ ሰረገላ ላይ ጫኑአት፥ በኮረብታውም ላይ ከነበረው ከአሚናዳብ ቤት አመጡአት፤ የአሚናዳብ ልጆችም ዖዛና ወንድሞቹ ታቦቷ ያለችበትን ሰረገላ ይነዱ ነበር።
ወደ ናኮንም አውድማ ደረሱ፤ ዖዛም በሬዎቹ አነቃንቀዋት ነበርና ይይዛት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ታቦት እጁን ዘረጋ፤ አስተካከላትም። ሲይዛትም በሬው ወጋው።
ታቦቱንም፥ ገበታውንም፥ መቅረዙንም፥ መሠዊያዎቹንም፥ የሚያገለግሉበትንም የመቅደሱን ዕቃ፥ መጋረጃውንም፥ ማገልገያውንም ሁሉ ይጠብቃሉ።