የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘኍል 7:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዐሥራ ሁለቱ የእ​ስ​ራ​ኤል አለ​ቆች፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች አለ​ቆች፥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን አቀ​ረቡ፤ እነ​ዚ​ህም ከተ​ቈ​ጠ​ሩት በላይ የተ​ሾሙ የነ​ገ​ዶች አለ​ቆች ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም የእስራኤል አለቆች ሆነው ከተቈጠሩት ነገዶች ኀላፊዎች የነበሩት የየቤተ ሰቡ መሪዎች ስጦታቸውን አቀረቡ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከተቈጠሩት በላይ የተሾሙት የነገዶች አለቆች የነበሩት የእስራኤል አለቆች፥ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ቁርባናቸውን አቀረቡ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚያ በኋላ በእስራኤል ነገዶች መካከል የጐሣ አለቆች የሆኑት ማለትም በሕዝብ ቈጠራ ጊዜ ኀላፊነት የነበራቸው ሁሉ፥

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእስራኤል አለቆች፥ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ ቍርባናቸውን አቀረቡ፤ እነዚህም ከተቈጠሩት በላይ የተሾሙ የነገዶች አለቆች ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘኍል 7:2
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሰሎ​ሞ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤትና የራ​ሱን ቤተ መን​ግ​ሥት ሠርቶ ከፈ​ጸመ ከሃያ ዓመት በኋላ ያን​ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ታቦት ከዳ​ዊት ከተማ ከጽ​ዮን ያወጡ ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና የነ​ገድ አለ​ቆ​ችን ሁሉ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ቤቶች መሳ​ፍ​ንት ንጉሡ ሰሎ​ሞን በጽ​ዮን ሰበ​ሰ​ባ​ቸው።


አለ​ቆ​ቹም ለሕ​ዝ​ቡና ለካ​ህ​ናቱ፥ ለሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም በፈ​ቃ​ዳ​ቸው ሰጡ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አለ​ቆች፥ ኬል​ቅ​ያስ፥ ዘካ​ር​ያስ፥ ኢዮ​ሔል፥ ለፋ​ሲ​ካው መሥ​ዋ​ዕት እን​ዲ​ሆን ሁለት ሺህ ስድ​ስት መቶ በጎ​ች​ንና ፍየ​ሎ​ችን፥ ሦስት መቶም በሬ​ዎ​ችን ለካ​ህ​ናቱ ሰጡ።


አለ​ቆ​ችም የመ​ረ​ግድ ድን​ጋ​ይና የተ​ቀ​ረጸ ድን​ጋ​ይን ለል​ብሰ መት​ከ​ፍና ለል​ብሰ እን​ግ​ድዓ የሚ​ገ​ቡ​ት​ንም ፈር​ጦ​ችን፥


ሙሴም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ነገ​ዶች አለ​ቆች እን​ዲህ ብሎ ነገ​ራ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘው ነገር ይህ ነው።


ሙሴና ካህኑ አል​ዓ​ዛ​ርም ወር​ቁ​ንና በልዩ ልዩ የተ​ሠ​ራ​ውን ዕቃ ሁሉ ከእ​ጃ​ቸው ተቀ​በሉ።