የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘኍል 5:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ያች ሰው​ነት ብት​ና​ዘዝ፥ ያደ​ረ​ገ​ች​ው​ንም ኀጢ​አት ሁሉ ብት​ና​ገር የወ​ሰ​ደ​ውን ዓይ​ነ​ቱን ሁሉ ይመ​ልስ። አም​ስ​ተኛ እጅም ለባለ ገን​ዘቡ ይጨ​ምር።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በሠራው ኀጢአት ይናዘዝ፤ ስለ በደሉም ሙሉ ካሳ ይክፈል፤ የተመደበበትም ካሳ ላይ አንድ ዐምስተኛ በመጨመር በደል ላደረሰበት ሰው ይስጥ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የሠራውንም ኃጢአት ይናዘዝ፤ የወሰደውንም በሙሉ ይመልስ፥ በእርሱም ላይ አምስት እጅ ይጨምርበት፥ ለበደለውም ሰው ይስጠው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኃጢአቱን ይናዘዝ፤ ስለ በደል ሊከፈል በሚገባው ዋጋ ላይ ከመቶ ኻያ እጅ በመጨመር ለተበደለው ሰው ካሳ ይስጥ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የወሰደውንም በሙሉ ይመልስ አምስተኛውንም ይጨምርበት፥ ለበደለውም ሰው ይስጠው።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘኍል 5:7
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድ​ቅ​ንና ምጽ​ዋ​ትን ይወ​ድ​ዳል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ር​ታው ምድ​ርን ሞላ።


“እንደ ከዱኝ፥ ቸልም እን​ዳ​ሉኝ፥ በፊ​ቴም አግ​ድ​መው እንደ ሄዱ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንና፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ኀጢ​አት ይና​ዘ​ዛሉ።


እኔም ደግሞ አግ​ድሜ ከእ​ነ​ርሱ ጋር በቍጣ ሄድሁ፤ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ምድር አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ። ነገር ግን በዚ​ያን ጊዜ ያል​ተ​ገ​ረ​ዘው ልባ​ቸው ያፍ​ራል፤ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ይና​ዘ​ዛሉ፤


“ሰው ቢዘ​ነጋ፥ ሳያ​ው​ቅም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በተ​ቀ​ደ​ሰው በማ​ና​ቸ​ውም ነገር ኀጢ​አ​ትን ቢሠራ፥ ለበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከመ​ን​ጋዉ ነውር የሌ​ለ​በ​ትን እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን በብር ሰቅል የተ​ገ​መ​ተ​ውን አውራ በግ ለበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል።


በተ​ቀ​ደሰ ነገር ላይ ስለ ሠራው ኀጢ​አት ዕዳ ይከ​ፍ​ላል፤ አም​ስ​ተ​ኛ​ው​ንም እጅ ይጨ​ም​ር​በ​ታል፤ ለካ​ህ​ኑም ይሰ​ጠ​ዋል። ካህ​ኑም በበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት አውራ በግ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይቅር ይባ​ል​ለ​ታል።


ከእ​ነ​ዚህ ነገ​ሮች በአ​ን​ዲቱ በደ​ለኛ ቢሆን፥ የሠ​ራ​ውን ኀጢ​አት ይና​ዘ​ዛል።


የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት እንደ ሆነ እን​ዲሁ የበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ነው፤ ለሁ​ለቱ አንድ ሕግ ነው፤ በእ​ነ​ርሱ የሚ​ያ​ስ​ተ​ሰ​ርይ ካህን ይወ​ስ​ደ​ዋል።


ነገር ግን ይመ​ል​ስ​ለት ዘንድ ሰው​ዬው ዘመድ ባይ​ኖ​ረው፥ ስለ በደል ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​መ​ል​ሰው ነገር ለካ​ህኑ ይሁን፤ ይህም ስለ እርሱ ማስ​ተ​ስ​ረያ ከሚ​ደ​ረ​ግ​በት አውራ በግ ላይ ይጨ​መር።


ዘኬ​ዎ​ስም ቆመና ጌታ​ች​ንን እን​ዲህ አለው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ አሁን የገ​ን​ዘ​ቤን እኩ​ሌታ ለነ​ዳ​ያን እሰ​ጣ​ለሁ፤ የበ​ደ​ል​ሁ​ትም ቢኖር ስለ አንድ ፋንታ አራት እጥፍ እከ​ፍ​ለ​ዋ​ለሁ።”


ኢያ​ሱም አካ​ንን፥ “ልጄ ሆይ! ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ስጥ፤ ለእ​ር​ሱም ተና​ዘዝ፤ ያደ​ረ​ግ​ኸ​ው​ንም ንገ​ረኝ፤ አት​ሸ​ሽ​ገ​ኝም” አለው።