ዘኍል 3:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በክህነት ያገለግሉ ዘንድ የተቀቡና እጆቻቸውን የተቀደሱ የአሮን ልጆች ስም ይህ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ለክህነት አገልግሎት የለያቸው፣ ካህናት ለመሆን የተቀቡት የአሮን ወንድ ልጆች ስም ይህ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአሮን ልጆች፥ እርሱም በክህነት አገልግሎት እንዲያገለግሉ የቀደሳቸው፥ የተቀቡ ካህናት ስሞቻቸው እነዚህ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህም በክህነት እንዲያገለግሉ ተቀብተው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተቀቡ ካህናት በክህነትም ያገለግሉ ዘንድ የቀደሳቸው የአሮን ልጆች ስም ይህ ነው። |
ይህንም ሁሉ ወንድምህን አሮንን፥ ከእርሱም ጋር ልጆቹን ታለብሳቸዋለህ፤ በክህነት እንዲያገለግሉኝ ትቀባቸዋለህ፤ እጆቻቸውንም ታነጻለህ፤ ትቀድሳቸውማለህ።
አባታቸውን እንደ ቀባህ ትቀባቸዋለህ፤ ካህናትም ይሆኑኛል። ይህም ለልጅ ልጃቸው ለዘለዓለም የክህነት ቅብዐት ይሆንላቸዋል።”
ሙሴም ከቅብዐቱ ዘይትና በመሠዊያው ላይ ከአለው ከደሙ ወስዶ በአሮንና በልብሱ ላይ ፥ በልጆቹና በልጆቹ ልብስ ላይ ረጨው፤ አሮንንና ልብሱንም፥ ልጆቹንም፥ የልጆቹንም ልብስ ቀደሰ።
ናዳብና አብዩድ በሲና ምድረ በዳ በእግዚአብሔር ፊት ከሌላ እሳት ጭረው አምጥተዋልና በእግዚአብሔር ፊት ሞቱ፤ ልጆችም አልነበሩአቸውም። አልዓዛርና ኢታምር ከአባታቸው ከአሮን ጋር በክህነት ያገለግሉ ነበር።
ኦሪትስ የሚሞት ሰውን ሊቀ ካህናት አድርጋ ትሾማለች፤ ከኦሪት በኋላ የመጣው የእግዚአብሔር የመሐላ ቃሉ ግን ዘለዓለም የማይለወጥ ፍጹም ወልድን ካህን አድርጎ ሾመልን።