የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘኍል 28:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለእ​ህ​ልም ቍር​ባን የኢን መስ​ፈ​ሪያ አራ​ተኛ እጅ በሆነ፥ ተወ​ቅጦ በተ​ጠ​ለለ ዘይት የተ​ለ​ወሰ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ዐሥ​ረኛ እጅ መል​ካም ዱቄት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚህም ጋራ ተወቅጦ በተጠለለ በሂን አንድ አራተኛ የወይራ ዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ ዐሥረኛ ልም ዱቄት የእህል ቍርባን አዘጋጁ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የኢንም መስፈሪያ አራተኛ እጅ በሆነ ተወቅጦ በተጠለለ ዘይት የተለወሰ የኢፍ መስፈሪያ አሥረኛ እጅ መልካም ዱቄት ለእህል ቁርባን ታቀርባለህ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከእያንዳንዱም ጠቦት ጋር ምርጥ በሆነ፥ በአንድ ሊትር የወይራ ዘይት የተለወሰ፥ አንድ ኪሎ ዱቄት የእህል ቊርባን ሆኖ ይቅረብ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለእህልም ቍርባን የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ በሆነ ተወቅጦ በተጠለለ ዘይት የተለወሰ የኢፍ መስፈሪያ አሥረኛ እጅ መልካም ዱቄት ታቀርባለህ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘኍል 28:5
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወደ ፊኒ​ቆ​ንም ምድር እስ​ኪ​መጡ ድረስ መና በሉ። ጎሞ​ርም የሦ​ስት ላዳን መስ​ፈ​ሪያ ዐሥ​ረኛ ክፍል ነው።


ከእ​ር​ሱም ጋር የእ​ህ​ልን ቍር​ባን፥ በኢን መስ​ፈ​ሪያ ሢሶ ዘይት የተ​ለ​ወሰ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ስድ​ስ​ተኛ እጅ የስ​ንዴ ዱቄ​ትን፤ በየ​ማ​ለ​ዳው ታቀ​ር​ባ​ለህ፤ ይህ የሚ​ደ​ረግ ዘለ​ዓ​ለ​ማዊ ሥር​ዐት ነው።


“ማና​ቸ​ውም ሰው ቍር​ባን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት እን​ዲ​ሆን ቢያ​ቀ​ርብ፥ ቍር​ባኑ ከመ​ል​ካም ስንዴ ዱቄት ይሁን፤ ዘይ​ትም ያፈ​ስ​ስ​በ​ታል፤ ነጭ ዕጣ​ንም ይጨ​ም​ር​በ​ታል፤ ይህም መሥ​ዋ​ዕት ነው።


አን​ዱን ጠቦት በማ​ለዳ፥ ሌላ​ው​ንም ጠቦት በማታ አቅ​ርቡ፤


በእ​ሳት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን የቀ​ረበ፥ በሲና ተራራ የተ​ሠራ ለዘ​ወ​ትር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነው።


መባ​ውም ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት የተ​ሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛ​ኑም ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ድስት፤