የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘኍል 25:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሙሴም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሕዝ​ቦች፥ “እና​ንተ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችሁ ብዔል ፌጎ​ርን የተ​ከ​ተ​ሉ​ትን ሰዎ​ቻ​ች​ሁን ግደሉ” አላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሙሴም የእስራኤልን ዳኞች፣ “እያንዳንዳችሁ በኣል ፌጎርን በማምለክ የተባበሩትን ሰዎቻችሁን ግደሉ አላቸው።”

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሙሴም የእስራኤልን ዳኞች፦ “እናንተም እያንዳንዳችሁ ብዔልፌጎርን የተከተሉትን ሰዎቻችሁን ግደሉ” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሙሴም ለእስራኤል መሪዎች “እያንዳንዳችሁ ከየነገዳችሁ በዓል ለሚባለው የፒዖር ጣዖት የሰገደውን ሰው ሁሉ ግደሉ” ብሎ ትእዛዝ አስተላለፈ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሙሴም የእስራኤልን ዳኞች፦ እናንተ ሁሉ ብዔልፌጎርን የተከተሉትን ሰዎቻችሁን ግደሉ አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘኍል 25:5
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኤል​ያ​ስም ሕዝ​ቡን፥ “የበ​ዓ​ልን ነቢ​ያት ያዙ፤ ከእ​ነ​ርሱ አንድ ሰው እን​ኳን የሚ​ያ​መ​ልጥ አይ​ኑር፤” አላ​ቸው። ያዙ​አ​ቸ​ውም፤ ኤል​ያ​ስም ወደ ቂሶን ወንዝ ወስዶ፥ በዚያ እየ​ወጋ ጣላ​ቸው።


አን​ተም ከሕ​ዝቡ ሁሉ ኀያ​ላን ሰዎ​ችን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ሩ​ትን እው​ነ​ተ​ኞች ሰዎ​ችን፥ ትዕ​ቢ​ት​ንም የሚ​ጠሉ ሰዎ​ችን ፈልግ። ከእ​ነ​ር​ሱም የሺህ አለ​ቆ​ችን፥ የመቶ አለ​ቆ​ችን፥ የአ​ምሳ አለ​ቆ​ችን፥ የዐ​ሥ​ርም አለ​ቆ​ችን ሹም​ላ​ቸው።


“ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቻ በቀር ለአ​ማ​ል​ክት የሚ​ሠዋ ፈጽሞ ይጥፋ።


እስ​ራ​ኤ​ልም ለብ​ዔል ፌጎር ራሳ​ቸ​ውን ለዩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ፈጽሞ ተቈጣ።


ክፋ​ተ​ኞች ሰዎች ከእ​ና​ንተ ዘንድ ወጥ​ተው፦ ሄደን የማ​ታ​ው​ቋ​ቸ​ውን ሌሎች አማ​ል​ክት እና​ም​ልክ ብለው የከ​ተ​ማ​ቸ​ውን ሰዎች አሳቱ ሲሉ ወሬ ብት​ሰማ፥


የዚ​ያ​ችን ሀገር ሰዎች በሰ​ይፍ ስለት ፈጽሞ ትመ​ታ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ሀገ​ሪ​ቱን፥ በው​ስ​ጥ​ዋም ያለ​ውን ሁሉ ትረ​ግ​ማ​ለህ።


“የአ​ባ​ትህ ወይም የእ​ና​ትህ ልጅ ወን​ድ​ምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ ወይም አብ​ራህ የም​ት​ተኛ ሚስ​ትህ ወይም እንደ ነፍ​ስህ ያለ ወዳ​ጅህ በስ​ውር፦ ና፥ ሄደን አን​ተም አባ​ቶ​ች​ህም የማ​ታ​ው​ቋ​ቸ​ውን ሌሎች አማ​ል​ክት እና​ም​ልክ ብሎ ቢያ​ስ​ትህ፥


ነገር ግን ፈጽ​መህ ተና​ገር፤ እር​ሱን ለመ​ግ​ደል በፊት ያንተ እጅ፥ ከዚ​ያም በኋላ የሕ​ዝቡ ሁሉ እጅ በላዩ ትሁን።


እኛ እስከ ዛሬ ድረስ ከእ​ርሱ ያል​ነ​ጻ​ን​በት የፌ​ጎር ኀጢ​አት ጥቂት ነውን? በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማኅ​በር ላይ መቅ​ሠ​ፍት ወረደ።