የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘኍል 21:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሕ​ዝቡ ላይ የሚ​ገ​ድሉ እባ​ቦ​ችን ሰደደ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ነደፉ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ብዙ ሰዎች ሞቱ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር መርዘኛ እባቦች ሰደደባቸው፤ ሕዝቡን ነደፉ፤ ብዙ እስራኤላውያንም ሞቱ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታም በሕዝቡ ላይ እባቦችን ላከ፥ ሕዝቡንም ነደፉ፤ ከእስራኤልም ብዙ ሰዎች ሞቱ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር መርዘኛ እባብ ወደ ሕዝቡ ስለ ላከ ብዙ እስራኤላውያን ተነድፈው ሞቱ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ እባቦችን ሰደደ፥ ሕዝቡንም ነደፉ፤ ከእስራኤልም ብዙ ሰዎች ሞቱ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘኍል 21:6
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ፍል​ስ​ጥ​ኤም ሆይ፥ ከእ​ባቡ ዘር እፉ​ኝት ይወ​ጣ​ልና፥ ፍሬ​ውም የሚ​በ​ር​ርና እሳት የሚ​መ​ስል እባብ ይሆ​ና​ልና፥ የኀ​ይ​ላ​ችሁ ቀን​በር ተሰ​ብ​ሮ​አ​ልና ሁላ​ች​ሁም ደስ አይ​በ​ላ​ችሁ።


ተባ​ትና እን​ስት አን​በሳ፥ እፉ​ኝ​ትም፥ ነዘር እባ​ብም፥ በሚ​ወ​ጡ​ባት በመ​ከ​ራና በጭ​ን​ቀት ምድር በኩል ብል​ጽ​ግ​ና​ቸ​ውን በአ​ህ​ዮች ጫንቃ ላይ፥ መዛ​ግ​ብ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በግ​መ​ሎች ሻኛ ላይ እየ​ጫኑ ወደ​ማ​ይ​ጠ​ቅ​ሙ​አ​ቸው ሕዝብ ይሄ​ዳሉ።


እነሆ አስ​ማት የማ​ይ​ከ​ለ​ክ​ላ​ቸ​ውን የሚ​ገ​ድሉ እባ​ቦ​ችን እሰ​ድ​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይነ​ድ​ፉ​አ​ች​ኋል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በዚ​ያች ሀገር ላይ ክፉ አው​ሬን ባመጣ፥ ፈጽ​ሜም ባጠ​ፋት በዚ​ያም አውሬ ፊት የሚ​ያ​ልፍ ባይ​ገኝ፥


ከእ​ነ​ር​ሱም አን​ዳ​ን​ዶቹ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እንደ ተፈ​ታ​ተ​ኑት፥ ነዘር እባ​ብም እንደ አጠ​ፋ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አን​ፈ​ታ​ተን።


የሚ​ና​ደፍ እባ​ብና ጊንጥ፥ ጥማ​ትም ባለ​ባት፥ ውኃም በሌ​ለ​ባት፥ በታ​ላ​ቂ​ቱና በም​ታ​ስ​ፈ​ራው ምድረ በዳ የመ​ራ​ህን፥ ከጭ​ንጫ ድን​ጋ​ይም ጣፋጭ ውኃን ያወ​ጣ​ል​ህን፥