የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘኍል 20:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እኛ፥ ከብ​ቶ​ቻ​ች​ንም በዚያ እን​ሞት ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማኅ​በር ወደ​ዚህ ምድረ በዳ ለምን አወ​ጣ​ችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የእግዚአብሔርን ማኅበረ ሰብ ወደዚህ ምድረ በዳ ያመጣችሁት ለምንድን ነው! ከነከብቶቻችን እዚሁ እንድናልቅ ነውን?

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እኛም ከብቶቻችንም በዚህ እንድንሞት የጌታን ጉባኤ ወደዚህ ምድረ በዳ ለምን አመጣችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የእግዚአብሔርን ማኅበር ወደዚህ ምድረ በዳ ያመጣችሁት እኛና እንስሶቻችን እዚህ እንድናልቅ ለማድረግ ነውን?

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እኛ ከብቶቻችንም በዚያ እንሞት ዘንድ የእግዚአብሔርን ጉባኤ ወደዚህ ምድረ በዳ ለምን አመጣችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት



ዘኍል 20:4
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምሕ​ረት ለሰው ልጆ​ችም ያደ​ረ​ገ​ውን ድን​ቁን ንገሩ፤


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አሉ​አ​ቸው፥ “በሥ​ጋው ምን​ቸት አጠ​ገብ ተቀ​ም​ጠን እስ​ክ​ን​ጠ​ግብ ድረስ እን​ጀ​ራና ሥጋ በም​ን​በ​ላ​በት ጊዜ በግ​ብፅ ምድር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ምነው በሞ​ትን! ይህን ጉባኤ ሁሉ በራብ ልት​ገ​ድሉ እኛን ወደ​ዚች ምድረ በዳ አም​ጥ​ታ​ች​ኋ​ልና።”


ሕዝ​ቡም በዚያ ስፍራ ውኃ ተጠሙ፥ “እኛ​ንና ልጆ​ቻ​ች​ንን፥ ከብ​ቶ​ቻ​ች​ን​ንም በጥ​ማት ልት​ገ​ድል ለምን ከግ​ብፅ አወ​ጣ​ኸን?” ሲሉ በሙሴ ላይ አን​ጐ​ራ​ጐሩ።


እነ​ር​ሱም፥ “በፈ​ር​ዖ​ንና በሹ​ሞቹ ፊት ሽታ​ች​ንን አግ​ም​ታ​ች​ሁ​ታ​ልና፥ ይገ​ድ​ለ​ንም ዘንድ ሰይ​ፍን በእጁ ሰጥ​ታ​ች​ሁ​ታ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ል​ከ​ታ​ችሁ፤ ይፍ​ረ​ድ​ባ​ች​ሁም” አሉ​አ​ቸው።


ነገር ግን በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ያለ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ንቃ​ች​ኋ​ልና፥ በፊ​ቱም፦ ለምን ከግ​ብፅ አወ​ጣ​ኸን? ብላ​ችሁ አል​ቅ​ሳ​ች​ኋ​ልና በአ​ፍ​ን​ጫ​ችሁ እስ​ኪ​ወጣ መር​ዝም እስ​ኪ​ሆ​ን​ባ​ችሁ ድረስ ወር ሙሉ ትበ​ሉ​ታ​ላ​ችሁ።”


በግ​ብፅ ያለ ዋጋ እን​በ​ላው የነ​በ​ረ​ውን ዓሣ፥ ዳቦ​ው​ንም፥ በጢ​ኹ​ንም፥ ኩራ​ቱ​ንም፥ ቀዩ​ንም ሽን​ኩ​ርት፥ ነጩ​ንም ሽን​ኩ​ርት ቍንዶ በር​በ​ሬ​ው​ንም እና​ስ​ባ​ለን።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ በሙ​ሴና በአ​ሮን ላይ አጕ​ረ​መ​ረሙ፤ ማኅ​በ​ሩም ሁሉ፥ “በዚህ ምድረ በዳ ከም​ን​ሞት በግ​ብፅ ምድር ሳለን ብን​ሞት በተ​ሻ​ለን ነበር።


በነ​ጋ​ውም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ፥ “እና​ንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕዝብ ገድ​ላ​ች​ኋል” ብለው በሙ​ሴና በአ​ሮን ላይ አጕ​ረ​መ​ረሙ።


“በእኛ ላይ አለ​ቃና ፈራጅ ማን አድ​ር​ጎ​ሃል? ብለው የካ​ዱ​ትን ያን ሙሴን በቍ​ጥ​ቋ​ጦው መካ​ከል በታ​የው በመ​ል​አኩ እጅ እር​ሱን መል​እ​ክ​ተ​ኛና አዳኝ አድ​ርጎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላከው።


ነገር ግን እስ​ራ​ኤል በም​ድረ በዳ እስከ ኤር​ትራ ባሕር ሄዱ፤ ወደ ቃዴ​ስም ደረሱ፤