Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 16:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

41 በነ​ጋ​ውም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ፥ “እና​ንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕዝብ ገድ​ላ​ች​ኋል” ብለው በሙ​ሴና በአ​ሮን ላይ አጕ​ረ​መ​ረሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

41 በማግስቱም መላው የእስራኤል ማኅበረ ሰብ፣ “እናንተ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ገድላችኋል” በማለት በሙሴና በአሮን ላይ አጕረመረሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

41 በማግስቱም የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ፦ “እናንተ የጌታን ሕዝብ ገድላችኋል” ብለው በሙሴና በአሮን ላይ አጉረመረሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

41 በማግስቱ መላው የእስራኤል ማኅበር “የእግዚአብሔር ወገኖች የሆኑትን ሕዝብ ገድላችኋል” በማለት በሙሴና በአሮን ላይ አጒረመረሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

41 በነጋውም የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ፦ እናንተ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ገድላችኋል ብለው በሙሴና በአሮን ላይ አጕረመረሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 16:41
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በመ​ር​ከ​ቦች ወደ ባሕር የሚ​ወ​ርዱ፥ በብዙ ውኃ ሥራ​ቸ​ውን የሚ​ሠሩ፥


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ በሙ​ሴና በአ​ሮን ላይ አጕ​ረ​መ​ረሙ፤ ማኅ​በ​ሩም ሁሉ፥ “በዚህ ምድረ በዳ ከም​ን​ሞት በግ​ብፅ ምድር ሳለን ብን​ሞት በተ​ሻ​ለን ነበር።


እየ​ጮ​ሁም እን​ዲህ አሉ፥ “እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች ሆይ፥ ርዱን፤ በየ​ስ​ፍ​ራው ሕዝ​ባ​ች​ንን፥ ኦሪ​ት​ንም፥ ይህ​ንም ስፍራ የሚ​ቃ​ወም ትም​ህ​ርት ለሰው ሁሉ የሚ​ያ​ስ​ተ​ምር እነሆ፥ ይህ ሰው ነው፤ አሁ​ንም አረ​ማ​ው​ያ​ንን ወደ መቅ​ደስ አስ​ገባ፤ ቤተ መቅ​ደ​ስ​ንም አረ​ከሰ።


“በኢ​የ​ሱስ ስም ለማ​ንም እን​ዳ​ታ​ስ​ተ​ምሩ ከል​ክ​ለ​ና​ችሁ አል​ነ​በ​ረ​ምን? እነሆ፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን በት​ም​ህ​ር​ታ​ችሁ ሞላ​ች​ኋት፤ የዚ​ያ​ንም ሰው ደም በእኛ ላይ ታመ​ጡ​ብን ዘንድ ትሻ​ላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው።


“ቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ።


የቤ​ቴ​ልም ካህን አሜ​ስ​ያስ ወደ እስ​ራ​ኤል ንጉሥ ወደ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ልኮ፥ “አሞጽ በእ​ስ​ራ​ኤል ቤት መካ​ከል ዐም​ፆ​ብ​ሃል፤ ምድ​ሪ​ቱም ቃሉን ሁሉ ልት​ሸ​ከም አት​ች​ልም” አለ።


አቤቱ፥ ከፍ ያለች ክን​ድ​ህን አላ​ወ​ቁም፤ ካወቁ ግን ያፍ​ራሉ። አላ​ዋ​ቆች ሰዎ​ችን ቅን​አት ያዛ​ቸው፤ አሁ​ንም እሳት ጠላ​ቶ​ችን ትበ​ላ​ለች።


በተ​ጨ​ነቁ ጊዜ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፥ ከመ​ከ​ራ​ቸ​ውም አዳ​ና​ቸው።


አክ​ዓ​ብም ኤል​ያ​ስን ባየው ጊዜ፥ አክ​ዓብ ኤል​ያ​ስን፥ “እስ​ራ​ኤ​ልን የም​ት​ገ​ለ​ባ​ብጥ አንተ ነህን?” አለው።


በክ​ብ​ርና በው​ር​ደት፥ በም​ር​ቃ​ትና በር​ግ​ማን፥ እንደ አሳ​ቾች ስን​ታይ እው​ነ​ተ​ኞች ነን።


ነገር ግን ከለ​ዳ​ው​ያን እን​ዲ​ገ​ድ​ሉን ወደ ባቢ​ሎ​ንም እን​ዲ​ያ​ፈ​ል​ሱን በእ​ጃ​ቸው አሳ​ል​ፈህ ትሰ​ጠን ዘንድ የኔ​ርዩ ልጅ ባሮክ በላ​ያ​ችን ላይ አነ​ሣ​ሥ​ቶ​ሃል” አሉት።


አለ​ቆ​ቹም ንጉ​ሡን፥ “ይህን የመ​ሰ​ለ​ውን ቃል ሲነ​ግ​ራ​ቸው በዚ​ያች ከተማ የቀ​ሩ​ትን የሰ​ል​ፈ​ኞ​ቹን እጅ፥ የሕ​ዝ​ቡ​ንም ሁሉ እጅ ያደ​ክ​ማ​ልና ይህ ሰው ይገ​ደል፤ ለዚህ ሕዝብ ክፋ​ትን እንጂ ሰላ​ምን አይ​መ​ኝ​ለ​ት​ምና” አሉት።


ከእ​ነ​ር​ሱም አን​ዳ​ን​ዶቹ እን​ዳ​ን​ጐ​ራ​ጐ​ሩ​በት፥ በመ​ቅ​ሠ​ፍ​ትም እን​ደ​ጠፉ አና​ን​ጐ​ራ​ጕር።


እነዚህ እንደ ምኞታቸው እየሄዱ የሚያንጎራጉሩና ስለ ዕድላቸው የሚያጕረመርሙ ናቸው፤ እንዲረባቸውም ለሰው ፊት እያደሉ አፋቸው ከመጠን ይልቅ ታላቅ ቃል ይናገራል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች