የእስራኤልም ልጆች አሉአቸው፥ “በሥጋው ምንቸት አጠገብ ተቀምጠን እስክንጠግብ ድረስ እንጀራና ሥጋ በምንበላበት ጊዜ በግብፅ ምድር በእግዚአብሔር እጅ ምነው በሞትን! ይህን ጉባኤ ሁሉ በራብ ልትገድሉ እኛን ወደዚች ምድረ በዳ አምጥታችኋልና።”
ማቴዎስ 4:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈታኝም ቀርቦ “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል!” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈታኙም ወደ ኢየሱስ ቀርቦ፣ “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፣ እነዚህን ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ እዘዝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈታኙ መጥቶ “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ እዘዝ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፈታኙ ወደ ኢየሱስ መጥቶ፥ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ፥ እስቲ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ እዘዝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈታኝም ቀርቦ፦ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል አለው። |
የእስራኤልም ልጆች አሉአቸው፥ “በሥጋው ምንቸት አጠገብ ተቀምጠን እስክንጠግብ ድረስ እንጀራና ሥጋ በምንበላበት ጊዜ በግብፅ ምድር በእግዚአብሔር እጅ ምነው በሞትን! ይህን ጉባኤ ሁሉ በራብ ልትገድሉ እኛን ወደዚች ምድረ በዳ አምጥታችኋልና።”
ኢየሱስ ግን ዝም አለ። ሊቀ ካህናቱም “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ የሆንህ እንደ ሆነ እንድትነግረን በሕያው እግዚአብሔር አምልሃለሁ፤” አለው።
መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፥ “መንፈስ ቅዱስ ያድርብሻል፤ የልዑል ኀይልም ይጋርድሻል፤ ከአንቺ የሚወለደውም ቅዱስ ነው፤ የልዑል እግዚአብሔር ልጅም ይባላል።
ሁሉም፥ “እንግዲያስ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህን?” አሉት፤ እርሱም፥ “እኔ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንሁ እናንተ ትላላችሁ” አላቸው።
ብዙ አጋንንትም፥ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነህ” እያሉና እየጮሁ ይወጡ ነበር፤ እርሱም ይገሥጻቸው ነበር፤ ክርስቶስም እንደ ሆነ ያውቁ ነበርና እንዲናገሩ አይፈቅድላቸውም ነበር።
ወደ ኢየሩሳሌምም ወስዶ በቤተ መቅደሱ የማዕዘን ጫፍ ላይ አቆመው፤ እንዲህም አለው፥ “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህስ አንተ ራስህ ወደ ታች መር ብለህ ውረድ።
ናትናኤልም፥ “በየት ታውቀኛለህ?” አለው፤ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፥ “ገና ፊልጶስ ሳይጠራህ በበለስ ዛፍ ሥር ሳለህ አይችሃለሁ” አለው።
ነገር ግን ይህ የተጻፈ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ እናንተ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ የዘለዓለም ሕይወትን ታገኙ ዘንድ ነው።
እኛ ማለት እኔ ጳውሎስ፥ ስልዋኖስና ጢሞቴዎስ የሰበክንላችሁ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ እውነትና ሐሰት አይደለም፤ ነገር ግን ስለ እርሱ ያስተማርነው እውነት ነው።
ከክርስቶስ ጋርም ተሰቀልሁ፤ ሕይወቴም አለቀች፤ ነገር ግን በክርስቶስ ሕይወት አለሁ፤ ዛሬም በሥጋዬ የምኖረውን ኑሮ የወደደኝን ስለ እኔም ራሱን አሳልፎ የሰጠውን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመን እኖራለሁ።
ስለዚህ እኔ ደግሞ ወደ ፊት እታገሥ ዘንድ ባልተቻለኝ ጊዜ “ፈታኝ ምናልባት ፈትኖአቸዋል፤ ድካማችንም ከንቱ ሆኖአል፤” ብዬ እምነታችሁን ለማወቅ ላክሁ።
እንግዲህ ወደ ሰማያት የወጣ ታላቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን፤ በእርሱ በማመን ጸንተን እንኑር።
አባት የለውም፤ እናትም የለችውም፤ ትውልዱም አይታወቅም፤ ለዘመኑ መጀመሪያ፥ ለሕይወቱም መጨረሻ የለውም፤ ክህነቱ የወልደ እግዚአብሔር ምሳሌ ሆኖ ለዘለዓለም ይኖራል።
ልትቀበለው ያለህን መከራ አትፍራ። እነሆ እንድፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያገባችሁ አለው፤ ዐሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ። እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ።