ኑ፤ እንጠበብባቸው፤ የበዙ እንደሆነ ጦርነት በመጣብን ጊዜ በጠላቶቻችን ላይ ተደርበው በኋላችን ይወጉናልና፥ ከምድራችንም ያስወጡናልና።”
ማቴዎስ 2:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገልን በስውር ጠርቶ ኮከቡ የታየበትን ዘመን ከእነርሱ በጥንቃቄ ተረዳ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሄሮድስ ጠቢባኑን በምስጢር አስጠርቶ በማነጋገር ኮከቡ የታየበትን ትክክለኛ ጊዜ ተረዳ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገልን በስውር ጠርቶ ኮከቡ የታየበትን ዘመን ከእነርሱ ተረዳ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ሄሮድስ እነዚያን የከዋክብት ተመራማሪዎች በስውር አስጠርቶ፥ ኮከቡ የታየበትን ትክክለኛ ጊዜ ጠይቆ ተረዳ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገልን በስውር ጠርቶ ኮከቡ የታየበትን ዘመን ከእነርሱ በጥንቃቄ ተረዳ፥ |
ኑ፤ እንጠበብባቸው፤ የበዙ እንደሆነ ጦርነት በመጣብን ጊዜ በጠላቶቻችን ላይ ተደርበው በኋላችን ይወጉናልና፥ ከምድራችንም ያስወጡናልና።”
አየዋለሁ፥ አሁን ግን አይደለም፤ እባርከዋለሁ፥ በቅርብ ግን አይደለም፤ ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል፤ ከእስራኤልም ሰው ይነሣል፥ የሞዓብንም አለቆች ይመታል፤ የሤትንም ልጆች ሁሉ ይማርካል።
ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል “የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና” እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።
ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ ተሣለቁበት ባየ ጊዜ እጅግ ተቆጣና ልኮ ከሰብአ ሰገል እንደ ተረዳው ዘመን በቤተ ልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን፥ ሁለት ዓመት የሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ።
ፊልክስ ግን አይሁድ ከጥንት ጀምሮ የክርስቲያንን ወገኖች ሕግና ትምህርት እንደሚቃወሙ ያውቅ ነበር፤ ስለዚህም “እንኪያስ የሺ አለቃው ሉስዮስ በመጣ ጊዜ ነገራችሁን እናውቅ ዘንድ እንመረምራለን” ብሎ ቀጠራቸው።
ሳኦልም፥ “እርስዋን እሰጠዋለሁ፤ እርስዋም እንቅፋት ትሆንበታለች” አለ። እነሆም፥ የፍልስጥኤማውያን እጅ በሳኦል ላይ ነበረች።