Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 18:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ሳኦ​ልም፥ “እር​ስ​ዋን እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ እር​ስ​ዋም እን​ቅ​ፋት ትሆ​ን​በ​ታ​ለች” አለ። እነ​ሆም፥ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ በሳ​ኦል ላይ ነበ​ረች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ሳኦልም በልቡ፣ “ወጥመድ እንድትሆነው፣ በፍልስጥኤማውያንም እጅ እንዲጠፋ እርሷን እድርለታለሁ” ሲል ዐሰበ። ስለዚህ ሳኦል ዳዊትን፣ “እነሆ፤ ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ዐማቼ ትሆናለህ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ሳኦልም በልቡ፥ “ወጥመድ እንድትሆነው፥ በፍልስጥኤማውያንም እጅ እንዲጠፋ እርሷን እድርለታለሁ” ሲል አሰበ። ስለዚህ ሳኦል ለሁለተኛ ጊዜ ዳዊትን፥ “እነሆ፤ ዛሬ ዐማቼ ትሆናለህ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 በልቡም “ሜልኮልን ለዳዊት እሰጣለሁ፤ እርስዋም ዳዊትን እንድታጠምድልኝ አደርጋለሁ፤ ከዚያም በኋላ በፍልስጥኤማውያን እጅ ይገደላል” ሲል አሰበ። ስለዚህም ሳኦል ለሁለተኛ ጊዜ ዳዊትን ጠርቶ “አሁን የእኔ ዐማች ትሆናለህ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ሳኦልም፦ ወጥመድ ትሆነው ዘንድ፥ የፍልስጥኤማውያንም እጅ በእርሱ ላይ ትሆን ዘንድ እርስዋን እድርለታለሁ አለ፥ ሳኦልም ዳዊትን፦ ዛሬ ሁለተኛ አማች ትሆነኛለህ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 18:21
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤቱ፥ ጸሎ​ቴን ስማ፥ ልመ​ና​ዬ​ንም አድ​ምጥ፥ ልቅ​ሶ​ዬ​ንም አድ​ምጥ፥ ቸልም አት​በ​ለኝ፤ እኔ በም​ድር ላይ መጻ​ተኛ ነኝና፥ እንደ አባ​ቶ​ችም ሁሉ እን​ግዳ ነኝና።


የፈ​ር​ዖ​ንም ሹሞች፥ “ይህ ሰው እስከ መቼ እን​ቅ​ፋት ይሆ​ን​ብ​ናል? አም​ላ​ካ​ቸ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ል​ኩት ዘንድ ሰዎ​ችን ልቀቅ፤ ግብ​ፅስ እንደ ጠፋች ገና አታ​ው​ቅ​ምን?” አሉት።


በሕ​ዝቤ መካ​ከል ክፉ​ዎች ሰዎች ተገ​ኝ​ተ​ዋል፤ ሰዎ​ች​ንም ይዘው ይገ​ድሉ ዘንድ ወጥ​መ​ድን ይዘ​ረ​ጋሉ።


ምላ​ሳ​ቸው የተ​ሳለ ፍላጻ ነው፤ ንግ​ግ​ራ​ቸው ሽን​ገላ ነው፤ ለባ​ል​ን​ጀ​ራ​ቸው ሰላ​ምን ይና​ገ​ራሉ፤ በል​ባ​ቸው ግን ጥላ​ቻን ይይ​ዛሉ።


ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን፥ “ታላ​ቂቱ ልጄ ሜሮብ እነ​ኋት፤ እር​ስ​ዋን እድ​ር​ል​ሃ​ለሁ፤ ብቻ ጀግና ልጅ ሁን​ልኝ፤ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጦር​ነት ተጋ​ደል” አለው። ሳኦ​ልም፥ “የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ በእ​ርሱ ላይ ትሁን እንጂ የእኔ እጅ በእ​ርሱ ላይ አት​ሁን” ይል ነበር።


ሳኦ​ልም ብላ​ቴ​ኖ​ቹን፥ “እነሆ፥ ንጉሥ እጅግ ወድ​ዶ​ሃል፤ ቤተ ሰቡም ሁሉ ወድ​ደ​ው​ሃል፤ አሁ​ንም ለን​ጉሥ አማች ሁን ብላ​ችሁ በስ​ውር ለዳ​ዊት ንገ​ሩት” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው።


የሳ​ኦ​ልም ብላ​ቴ​ኖች ይህን ቃል ለዳ​ዊት ነገ​ሩት፤ ለን​ጉ​ሥም አማች ይሆን ዘንድ ዳዊ​ትን ደስ አሰ​ኘው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች