የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ማቴዎስ 1:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እሴይም ንጉሥ ዳዊትን ወለደ፤ ንጉሥ ዳዊትም ከኦርዮ ሚስት ሰሎሞንን ወለደ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እሴይ ንጉሥ ዳዊትን ወለደ። ዳዊት የኦርዮ ሚስት ከነበረችው ሰሎሞንን ወለደ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እሴይ ንጉሥ ዳዊትን ወለደ፤ ዳዊትም ከኦርዮ ሚስት ሰሎሞንን ወለደ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እሴይ ንጉሥ ዳዊትን ወለደ። ንጉሥ ዳዊት የኦርዮ ሚስት ከነበረችው ሰሎሞንን ወለደ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እሴይም ንጉሥ ዳዊትን ወለደ። ንጉሥ ዳዊትም ከኦርዮ ሚስት ሰሎሞንን ወለደ፤

ምዕራፉን ተመልከት



ማቴዎስ 1:6
25 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊ​ትም ልኮ ስለ ሴቲቱ ጠየቀ፤ አንድ ሰውም፥ “የኤ​ል​ያብ ልጅ የኬ​ጤ​ያ​ዊው የኦ​ርዮ ሚስት ቤር​ሳ​ቤህ አይ​ደ​ለ​ች​ምን?” አለው።


የዳ​ዊ​ትም የመ​ጨ​ረሻ ቃሉ ይህ ነው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፍ ከፍ ያደ​ረ​ገው፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ የቀ​ባው፥ የታ​ማኙ ሰው፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ መል​ካም ባለ​መ​ዝ​ሙር የሆ​ነው፥ የታ​ማኙ የእ​ሴይ ልጅ የዳ​ዊት ንግ​ግር ይህ ነው፤


ኬጤ​ያ​ዊው ኦርዮ፤ ሁሉም በሁሉ ሠላሳ ሰባት ናቸው።


ከኬ​ጥ​ያ​ዊው ከኦ​ርዮ ነገር በቀር ዳዊት በዘ​መኑ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገ​ርን አድ​ርጎ ነበ​ርና፥ ካዘ​ዘ​ውም ነገር ሁሉ ፈቀቅ አላ​ለም ነበ​ርና።


ኬጢ​ያ​ዊው ዑር​ያስ፥ የአ​ሕ​ላይ ልጅ ዘባት፤


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የተ​ወ​ለ​ዱ​ለት የል​ጆቹ ስም ይህ ነው፤ ሳማ፥ ሶባብ፥ ናታን፥ ሰሎ​ሞን፤


ስድ​ስ​ተ​ኛ​ው​ንም አሶ​ንን፥ ሰባ​ተ​ኛ​ው​ንም ዳዊ​ትን ወለደ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ብዙ ልጆች ሰጥ​ቶ​ኛ​ልና ከል​ጆቼ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ዙፋን ላይ ተቀ​ምጦ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ይነ​ግሥ ዘንድ ልጄን ሰሎ​ሞ​ንን መር​ጦ​ታል።


እነ​ዚህ ደግሞ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ ከዓ​ሚል ልጅ ከቤ​ር​ሳ​ቤህ ስማዕ፥ ሶባብ፥ ናታን፥ ሰሎ​ሞን፥ አራት፤


ከእ​ን​ቅ​ልፍ እን​ደ​ሚ​ነቃ፥ አቤቱ፥ በከ​ተ​ማህ ምል​ክ​ታ​ቸ​ውን ታስ​ነ​ው​ራ​ለህ።


ከእ​ሴይ ሥር በትር ትወ​ጣ​ለች፤ አበ​ባም ከግ​ንዱ ይወ​ጣል።


ሰልሞንም ከራኬብ ቦኤዝን ወለደ፤ ቦኤዝም ከሩት ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፤


ስለ ሥጋ ደካ​ማ​ነት የኦ​ሪት ሕግ ከሞት ማዳን በተ​ሳ​ነው ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኀ​ጢ​ኣ​ተና ሥጋ ምሳሌ ልጁን ላከ፤ ያች​ንም ኀጢ​አት በሥ​ጋው ቀጣት።


ቦዔዝም ኢዮቤድን ወለደ፥ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፥ እሴይም ዳዊትን ወለደ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ እን​ዳ​ይ​ነ​ግሥ ለና​ቅ​ሁት ለሳ​ኦል የም​ታ​ለ​ቅ​ስ​ለት እስከ መቼ ነው? የዘ​ይ​ቱን ቀንድ ሞል​ተህ ና፤ በል​ጆቹ መካ​ከል ለእኔ ንጉሥ አዘ​ጋ​ጅ​ቼ​አ​ለ​ሁና ወደ እሴይ ወደ ቤተ ልሔም እል​ክ​ሃ​ለሁ” አለው።


ዳዊ​ትም የዚያ የኤ​ፍ​ራ​ታ​ዊው ሰው ልጅ ነበረ፤ ያም ሰው ከቤተ ልሔም ይሁዳ ስሙም እሴይ ነበረ፤ ስም​ንት ልጆ​ችም ነበ​ሩት፤ እሴ​ይም በሳ​ኦል ዘመን በዕ​ድሜ አር​ጅቶ ሸም​ግ​ሎም ነበር።


ሳኦ​ልም፥ “አንተ ብላ​ቴና የማን ልጅ ነህ?” አለው ዳዊ​ትም፥ “እኔ የቤተ ልሔሙ የባ​ሪ​ያህ የእ​ሴይ ልጅ ነኝ” ብሎ መለሰ።


ሁላ​ችሁ በላዬ ዶል​ታ​ችሁ ተነ​ሣ​ች​ሁ​ብኝ፤ ልጄ ከእ​ሴይ ልጅ ጋር ሲማ​ማል ማንም አል​ገ​ለ​ጠ​ል​ኝም፤ ከእ​ና​ን​ተም አንድ ለእኔ የሚ​ያ​ዝን የለም፤ ዛሬም እንደ ሆነው ሁሉ ልጄ አገ​ል​ጋ​ዬን እን​ዲ​ዶ​ልት ሲያ​ስ​ነ​ሣ​ብኝ ማንም አላ​ስ​ታ​ወ​ቀ​ኝም” አላ​ቸው።