ሉቃስ 8:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ ጌታችን ኢየሱስ በየከተማዉና በየመንደሩ ተመላለሰ፤ የእግዚአብሔርንም መንግሥት ሰበከላቸው፤ አስተማራቸውም፤ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርትም ከእርሱ ጋር ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት የምሥራች ቃል እየሰበከ በየከተማውና በየመንደሩ ዐለፈ። ዐሥራ ሁለቱም ከርሱ ጋራ ነበሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም በኋላ ኢየሱስ እየሰበከና ስለ እግዚአብሔር መንግሥት የምሥራች እያበሠረ በየከተማውና በየመንደሩ ያልፍ ነበር፤ ዐሥራ ሁለቱም ከእርሱ ጋር ነበሩ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ኢየሱስ በየከተማውና በየመንደሩ የእግዚአብሔርን መንግሥት እየሰበከና የምሥራች እያበሠረ ያልፍ ነበር፤ ዐሥራ ሁለቱም አብረውት ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህም በኋላ እየሰበከና ስለ እግዚአብሔር መንግሥት የምሥራች እየተናገረ በየከተማይቱ በየመንደሩም ያልፍ ነበር፤ |
ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ፥ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ፥ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ፥ በከተማዎችና በመንደሮች ሁሉ ይዞር ነበር።
ከዚህም በኋላ በአንድ ቀን ሕዝቡን በመቅደስ ሲያስተምራቸው፥ ወንጌልንም ሲነግራቸው፥ የካህናት አለቆች፥ ጻፎችና ሽማግሌዎች ተነሡበት።
“የእግዚአብሔር መንፈስ በላዬ ነው፤ ስለዚህ ቀብቶ ለድሆች የምሥራችን እነግራቸው ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን እሰብክላቸው ዘንድ፥ ያዘኑትንም ደስ አሰኛቸው ዘንድ፥ ዕውሮችም ያዩ ዘንድ፥ የተገፉትንም አድናቸው ዘንድ፥ የታሰሩትንም እፈታቸው ዘንድ፥ የቈሰሉትንም አድናቸው ዘንድ፥
ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ በኀይልም እንደ ቀባው፥ እየዞረም መልካም እንደ አደረገ፥ ሰይጣን ያሸነፋቸውንም እንደ ፈወሰ ታውቃላችሁ። እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበርና።