Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ሮሜ 10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ስለ ጳው​ሎስ ፈቃድ

1 ወን​ድ​ሞች፥ የእ​ኔስ የልቤ ምኞት፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የማ​ቀ​ር​በው ጸሎ​ትም እስ​ራ​ኤል እን​ዲ​ድኑ ነው።

2 ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲ​ቀኑ ምስ​ክ​ራ​ቸው እኔ ነኝና፤ ነገር ግን ዐው​ቀው አይ​ደ​ለም።

3 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጽድቅ አያ​ው​ቁ​አ​ት​ምና በራ​ሳ​ቸ​ውም ጽድቅ ጸን​ተው ሊኖሩ ወደዱ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድቅ ግን መገ​ዛት ተሳ​ና​ቸው።

4 የኦ​ሪት ጽድቅ ፍጻ​ሜስ ለሚ​ያ​ም​ኑ​በት ሁሉ በክ​ር​ስ​ቶስ ማመን ነው።

5 ሙሴም “የኦ​ሪ​ትን ጽድቅ መሥ​ራ​ትን የፈ​ጸመ ሁሉ በእ​ርሱ ይጸ​ድ​ቅ​በ​ታል” አለ።

6 የእ​ም​ነት ጽድቅ ግን እን​ዲህ ይላል፥ “በል​ብህ ወደ ሰማይ ማን ይወ​ጣል?” አት​በል፤ ከሰ​ማይ የወ​ረ​ደው ክር​ስ​ቶስ ነው።

7 “ወደ ጥል​ቁም ማን ይወ​ር​ዳል?” አት​በል፤ ከሙ​ታን ተለ​ይቶ የተ​ነ​ሣው ክር​ስ​ቶስ ነው።

8 መጽ​ሐፍ እን​ዲሁ፥ “ቃል ለል​ብ​ህም ለአ​ፍ​ህም ቀር​ቦ​ል​ሃል ይል የለ​ምን?” ይህም የም​ን​ሰ​ብ​ከው የእ​ም​ነት ቃል ነው።

9 ኢየ​ሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአ​ፍህ ብት​መ​ሰ​ክር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሙ​ታን ለይቶ እንደ አስ​ነ​ሣው በል​ብህ ብታ​ምን ትድ​ና​ለህ።

10 በልቡ የሚ​ያ​ምን ይጸ​ድ​ቃ​ልና፤ በአ​ፉም የሚ​መ​ሰ​ክር ይድ​ና​ልና።

11 መጽ​ሐፍ፥ “የሚ​ያ​ም​ን​በት ሁሉ አያ​ፍ​ርም” ብሎ​አል።

12 አይ​ሁ​ዳ​ዊ​ንና አረ​ማ​ዊን አል​ለ​የም፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባለ​ጸጋ ስለ​ሆነ ለለ​መ​ነው ሁሉ ይበ​ቃ​ልና።

13 “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም የሚ​ጠራ ሁሉ ይድ​ናል።”

14 ነገር ግን ያላ​መ​ኑ​በ​ትን እን​ዴት ይጠ​ሩ​ታል? ባል​ሰ​ሙ​ትስ እን​ዴት ያም​ናሉ? ያለ ሰባ​ኪስ እን​ዴት ይሰ​ማሉ?

15 “መል​ካ​ሙን የም​ሥ​ራች የሚ​ያ​ወሩ እግ​ሮ​ቻ​ቸው እን​ዴት ያማሩ ናቸው?” ተብሎ እንደ ተጻፈ ካል​ተ​ላኩ እን​ዴት ይሰ​ብ​ካሉ?

16 ነገር ግን ሁሉም የወ​ን​ጌ​ልን ትም​ህ​ርት የሰሙ አይ​ደ​ለም፤ ኢሳ​ይ​ያ​ስም፥ “አቤቱ፥ ምስ​ክ​ር​ነ​ታ​ች​ን​ንስ ማን አመነ? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ክንዱ ለማን ተገ​ለጠ?” ብሎ​አ​ልና።

17 ማመን ከመ​ስ​ማት ነው፤ መስ​ማ​ትም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ነው።

18 ነገር ግን እን​ዲህ እላ​ለሁ፤ በውኑ እስ​ራ​ኤል ብቻ አል​ሰ​ሙ​ምን? መጽ​ሐፍ “ነገ​ራ​ቸው በም​ድር ሁሉ ተሰማ፤ ቃላ​ቸ​ውም እስከ ዓለም ዳርቻ ደረሰ” ብሎ የለ​ምን?

19 እስ​ራ​ኤል ብቻ አል​ሰ​ሙ​ምን? ሙሴስ አስ​ቀ​ድሞ እን​ዲህ ብሎ​አ​ቸው የለ​ምን? “እኔ በማ​ያ​ስ​ተ​ውሉ ወገ​ኖች አስ​ቀ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወገን ባል​ሆ​ነ​ውም አስ​ቈ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።”

20 ኢሳ​ይ​ያ​ስም ደፍሮ፥ “ለአ​ል​ፈ​ለ​ጉኝ ተገ​ኘሁ፤ ለአ​ል​ጠ​የ​ቁ​ኝም ተገ​ለ​ጥ​ሁ​ላ​ቸው” ብሏል።

21 ለእ​ስ​ራ​ኤል ግን “ሁል​ጊዜ ከዳ​ተ​ኞ​ችና ወን​ጀ​ለ​ኞች ወደ​ሆ​ኑት ሕዝብ እጄን ዘረ​ጋሁ” ብሎ​አል።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች