ሉቃስ 7:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእኔም የማይሰናከል ብፁዕ ነው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእኔ የማይሰናከል ሁሉ ብፁዕ ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእኔም የማይሰናከል ብፁዕ ነው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእኔ የማይሰናከል የተባረከ ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእኔም የማይሰናከለው ሁሉ ብፁዕ ነው አላቸው። |
ስምዖንም ባረካቸው፤ እናቱን ማርያምንም እንዲህ አላት፤ “እነሆ፥ ይህ ሕፃን ከእስራኤል መካከል ለብዙዎች ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው፥ ለሚቃወሙትም ምልክት ይሆን ዘንድ የተሠየመ ነው፤
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “ሄዳችሁ ያያችሁትንና የሰማችሁትን ለዮሐንስ ንገሩት፤ ዕውሮች ያያሉ፤ አንካሶችም ይሄዳሉ፤ ለምጻሞችም ይነጻሉ፤ ደንቆሮችም ይሰማሉ፤ ሙታንም ይነሣሉ፤ ለድሆችም ወንጌል ይሰበካል።
የዮሐንስ ደቀ መዛሙርትም ከሄዱ በኋላ ለሕዝቡ ስለ መጥምቁ ዮሐንስ እንዲህ ይላቸው ጀመር፥ “ምን ልታዩ ወደ ምድረ በዳ ወጣችሁ? ከነፋስ የተነሣ የሚወዛወዝ ሸንበቆን ነውን?
ለሥጋዊ ሰው ግን የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ይመስለዋልና፥ አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለሆነ ሊያውቅ አይችልም።