በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲመላለስም ሁለት ወንድማማች ጴጥሮስ የሚሉትን ስምዖንን ወንድሙንም እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ፤ ዓሣ አጥማጆች ነበሩና።
ሉቃስ 5:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በባሕሩም ዳር ሁለት ታንኳዎች ቁመው አየ፤ ከእነርሱም ውስጥ ዓሣ አጥማጆች መረባቸውን ሊያጥቡ ወረዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ ሁለት ጀልባዎች በሐይቁ ዳርቻ ቆመው አየ፤ ዓሣ አጥማጆቹ ግን ከጀልባዎቹ ወርደው መረባቸውን ያጥቡ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በባሕሩ ዳርም ቆመው የነበሩትን ሁለት ታንኳዎች አየ፤ ዓሣ አጥማጆቹ ግን ወጥተው መረቦቻቸውን ያጥቡ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ በባሕሩ ዳር ተጠግተው የቆሙትን ሁለት ጀልባዎች አየ፤ ዓሣ አጥማጆቹ ግን ከጀልባዎቹ ወርደው መረቦቻቸውን ያጥቡ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በባሕር ዳርም ቆመው የነበሩትን ሁለት ታንኳዎች አየ፤ ዓሣ አጥማጆች ግን ከእነርሱ ውስጥ ወጥተው መረቦቻቸውን ያጥቡ ነበር። |
በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲመላለስም ሁለት ወንድማማች ጴጥሮስ የሚሉትን ስምዖንን ወንድሙንም እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ፤ ዓሣ አጥማጆች ነበሩና።
ከዚያም እልፍ ብሎ ሌሎችን ሁለት ወንድማማች የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ከአባታቸው ከዘብዴዎስ ጋር በታንኳ መረባቸውን ሲያበጁ አየ፤ ጠራቸውም።
ከሁለቱ ታንኳዎች ወደ አንዲቱ ታንኳ ወጣ፤ ይቺውም ታንኳ የስምዖን ነበረች፤ “ከምድር ጥቂት እልፍ አድርጋት” አለው፤ በታንኳዪቱም ውስጥ ተቀምጦ ሕዝቡን አስተማራቸው።