ሉቃስ 20:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሰው ነው ብንለውም ሕዝቡ ሁሉ በድንጋይ ይወግሩናል፤ ሁሉም ዮሐንስ ነቢይ እንደ ሆነ አምነውበታልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘ከሰው’ ብንል ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስ ነቢይ መሆኑን ስለሚያምኑ በድንጋይ ይወግሩናል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘ከሰዎች’ ብንል ግን ሕዝቡ ሁሉ በድንጋይ ይወግሩናል፤ ምክንያቱም ዮሐንስ ነቢይ እንደ ነበረ ሁሉም ያምኑ ነበርና” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘ከሰው ነው’ ብንል ደግሞ ሕዝቡ ሁሉም በዮሐንስ ነቢይነት ስለሚያምኑ በድንጋይ ይወግሩናል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሰው ብንል ግን ሕዝቡ ሁሉ ይወግሩናል፤ ዮሐንስ ነቢይ እንደ ነበረ ሁሉ ያምኑ ነበርና አሉ። |
ብዙዎችም ወደ እርሱ ሄደው፥ “ዮሐንስ ምንም ያደረገው ተአምራት የለም፤ ነገር ግን ዮሐንስ ስለዚህ ሰው የተናገረው ሁሉ እውነት ሆነ” አሉ።
ከዚህም በኋላ የቤተ መቅደሱ ሹም ከሎሌዎቹ ጋር ሔዶ አባብሎ አመጣቸው፤ በግድም አይደለም፤ በድንጋይ እንዳይደበድቧቸው ሕዝቡን ይፈሩ ነበርና።