የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ሉቃስ 18:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ራሳ​ቸ​ውን ለሚ​ያ​መ​ጻ​ድ​ቁና ባል​ን​ጀ​ራ​ቸ​ውን ለሚ​ንቁ እን​ዲህ ብሎ መሰ​ለ​ላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ራሳቸውን እንደ ጻድቃን በመቍጠር ለሚመኩና ሌሎቹን በንቀት ዐይን ለሚመለከቱ ሰዎች እንዲህ ሲል ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጻድቃን ነን በማለት በራሳቸው ለሚታመኑና ሌሎቹን ሁሉ በጣም ለሚንቁ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ቀጥሎም ኢየሱስ ጻድቃን ነን እያሉ ለሚመኩና ሌሎችንም ለሚንቁ ሰዎች፥ ይህን ምሳሌ ተናገረ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ጻድቃን እንደ ሆኑ በራሳቸው ለሚታመኑና ሌሎቹን ሁሉ በጣም ለሚንቁ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፥

ምዕራፉን ተመልከት



ሉቃስ 18:9
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“እኔ ንጹሕ ነኝና ከእኔ ራቁ፥ ወደ እኔም አት​ቅ​ረቡ” ይላሉ። ስለ​ዚ​ህም የቍ​ጣዬ ጢስ በዘ​መኑ ሁሉ እንደ እሳት ይነ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ዋል።


በቃሉ የም​ት​ን​ቀ​ጠ​ቀጡ ሆይ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ይከ​ብር ዘንድ፦ ደስ​ታ​ች​ሁም ይገ​ለጥ ዘንድ፥ እነ​ር​ሱም ያፍሩ ዘንድ የሚ​ጠ​ሏ​ች​ሁ​ንና የሚ​ጸ​የ​ፉ​አ​ች​ሁን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን በሏ​ቸው።


ካህ​ኑም በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ደዌ​ውን ያያል፤ እነ​ሆም፥ ቈረ​ቈሩ ባይ​ሰፋ፥ በው​ስ​ጡም ብጫ ጠጕር ባይ​ኖር፥ የቈ​ረ​ቈ​ሩም መልክ ወደ ቆዳው ባይ​ጠ​ልቅ፤ ይላ​ጫል፤


ራሱን ሊያ​ከ​ብር ባል​ን​ጀ​ራ​ው​ንም ሊንቅ ወድዶ፥ “ባል​ን​ጀ​ራዬ ማነው?” አለው።


ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም፥ “ይህስ ኀጢ​ኣ​ተ​ኞ​ችን ይቀ​በ​ላል፤ አብ​ሮ​አ​ቸ​ውም ይበ​ላል” ብለው አን​ጐ​ራ​ጐሩ።


እር​ሱም፥ “እና​ን​ተስ ለሰው ይም​ሰል ትመ​ጻ​ደ​ቃ​ላ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ልቡ​ና​ች​ሁን ያው​ቃል፤ በሰው ዘንድ የከ​በረ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ናቀ ይሆ​ና​ልና።


ፈሪ​ሳ​ዊ​ውም ቆመና እን​ዲህ ብሎ ጸለየ፦ ‘አቤቱ እንደ ሌሎች ሰዎች፥ እንደ ቀማ​ኞ​ችና እንደ ዐመ​ፀ​ኞች፥ እንደ አመ​ን​ዝ​ሮ​ችም፥ ወይም እን​ደ​ዚህ ቀራጭ ያላ​ደ​ረ​ግ​ኸኝ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።


ሁሉም አይ​ተው “ወደ ኀጢ​ኣ​ተኛ ሰው ቤት ሊውል ገባ” ብለው አን​ጐ​ራ​ጐሩ።


የጠ​ራው ፈሪ​ሳ​ዊም ባየ ጊዜ በልቡ ዐሰበ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ይህስ ነቢይ ቢሆን ኖሮ ይህቺ የም​ት​ዳ​ስ​ሰው ሴት ማን እንደ ሆነች፥ እን​ዴ​ትስ እንደ ነበ​ረች ባላ​ወ​ቀም ነበ​ርን? ኀጢ​አ​ተኛ ናትና።”


አይ​ሁ​ድም፥ “አንተ ሳም​ራዊ እንደ ሆንህ፥ ጋኔ​ንም እንደ አለ​ብህ መና​ገ​ራ​ችን በሚ​ገባ አይ​ደ​ለ​ምን?” ብለው ጠየ​ቁት።


እነ​ር​ሱም ሰደ​ቡት፤ እን​ዲ​ህም አሉት፥ “አንተ የእ​ርሱ ደቀ መዝ​ሙር ሁን፤ እኛስ የሙሴ ደቀ መዛ​ሙ​ርት ነን።


እነ​ር​ሱም መል​ሰው፥ “ራስህ በኀ​ጢ​ኣት የተ​ወ​ለ​ድህ አንተ እኛን ታስ​ተ​ም​ረ​ና​ለ​ህን?” አሉት፤ ወደ ውጭም አወ​ጡት።


እር​ሱም፦ ‘ሂድ ርቀው ወደ አሉ አሕ​ዛብ እል​ክ​ሃ​ለ​ሁና’ ” አለኝ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጽድቅ አያ​ው​ቁ​አ​ት​ምና በራ​ሳ​ቸ​ውም ጽድቅ ጸን​ተው ሊኖሩ ወደዱ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድቅ ግን መገ​ዛት ተሳ​ና​ቸው።


እን​ግ​ዲህ በወ​ን​ድ​ምህ ላይ የም​ት​ፈ​ርድ አንተ ምን​ድን ነህ? ወን​ድ​ም​ህ​ንስ የም​ት​ነ​ቅፍ አንተ ምን​ድን ነህ? ሁላ​ችን በክ​ር​ስ​ቶስ የፍ​ርድ ዙፋን ፊት እን​ቆ​ማ​ለ​ንና።


የሚ​በ​ላ​ውም የማ​ይ​በ​ላ​ውን አይ​ና​ቀው፤ የማ​ይ​በ​ላ​ውም የሚ​በ​ላ​ውን አይ​ን​ቀ​ፈው፤ ሁሉ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አው​ቆ​አ​ቸ​ዋ​ልና።


እኔም ቀድሞ ኦሪት ሳት​ሠራ ሕያው ነበ​ርሁ፤ የኦ​ሪት ትእ​ዛዝ በመ​ጣች ጊዜ ግን ኀጢ​አት ሕይ​ወ​ትን አገ​ኘች፤ እኔ ግን ሞትሁ።