የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ሉቃስ 12:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በጨ​ለማ የም​ት​ና​ገ​ሩት በብ​ር​ሃን ይሰ​ማል፤ በእ​ል​ፍ​ኝም ውስጥ በጆሮ የም​ት​ን​ሾ​ካ​ሾ​ኩት በሰ​ገ​ነት ይሰ​በ​ካል።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ በጨለማ ያወራችሁት ሁሉ በብርሃን ይሰማል፤ በእልፍኝም ውስጥ በጆሮ ያንሾካሾካችሁት በሰገነት በይፋ ይነገራል።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህ በጨለማ የተናገራችሁት ሁሉ በብርሃን ይሰማል፤ በእልፍኝም ውስጥ በጆሮ የምትናገሩት በሰገነት ላይ ይታወጃል።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ በጨለማ የተናገራችሁት ሁሉ በብርሃን ይሰማል፤ በዝግ ቤት ውስጥ በሹክሹክታ በጆሮ የተናገራችሁትም በሰገነት ላይ በይፋ ይነገራል።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ስለዚህ በጨለማ የምትናገሩት ሁሉ በብርሃን ይሰማል፥ በእልፍኝም ውስጥ በጆሮ የምትናገሩት በሰገነት ላይ ይሰበካል።

ምዕራፉን ተመልከት



ሉቃስ 12:3
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሰ​ማይ ዎፍ ቃል​ህን ያወ​ጣ​ዋ​ልና፥ ክንፍ ያለ​ውም ነገ​ር​ህን ያወ​ራ​ዋ​ልና በል​ብህ ዐሳብ እን​ኳን ቢሆን ንጉ​ሥን አት​ሳ​ደብ፥ በመ​ኝታ ቤት​ህም ባለ​ጠ​ጋን አት​ሳ​ደብ።


በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ፤ በጆሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ።


እኔ እላችኋለሁ፥ ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል፤


በሰገነትም ያለ በቤቱ ያለውን ሊወስድ አይውረድ፤