ሉቃስ 11:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰይጣንስ እርስ በርሱ ከተለያየ መንግሥቱ እንዴት ይጸናል? በአጋንንት አለቃ በብዔል ዜቡል አጋንንትን ያወጣል ትላላችሁና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰይጣንም እርስ በርሱ ከተከፋፈለ፣ መንግሥቱ እንዴት ይጸናል? አጋንንትን በብዔልዜቡል እንደማወጣ ትናገራላችሁና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰይጣንም ደግሞ እርስ በርሱ ቢለያይ መንግሥቱ እንዴት ይቆማል? እኔ አጋንንትን በብዔልዜቡል እንደማወጣ እናንተ ብላችኋልና፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሰይጣን እርስ በርሱ የሚለያይ ከሆነ የእርሱ መንግሥት እንዴት ጸንቶ መቆም ይችላል? እናንተ ግን ‘እርሱ አጋንንትን የሚያስወጣ በብዔልዜቡል ነው፤’ ትሉኛላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ አጋንንትን በብዔል ዜቡል እንዳወጣ ትላላችሁና ሰይጣን ደግሞ እርስ በርሱ ከተለያየ መንግሥቱ እንዴት ትቆማለች? |
ዝናውም ወደ ሶርያ ሁሉ ወጣ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይም ተይዘው የታመሙትን ሁሉ አጋንንትም ያደሩባቸውን በጨረቃም የሚነሣባቸውን ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፤ ፈወሳቸውም።
ነገር ግን ከመካከላቸው፥ “በአጋንንት አለቃ በብዔል ዜቡል አጋንንትን ያወጣቸዋል” ያሉ ነበሩ፤ እርሱም መልሶ፥ “ሰይጣን ሰይጣንን ማውጣት እንደምን ይቻለዋል?” አላቸው።