ኢያሱ 8:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚያም ከከተማ ወጥተው ተቀበሉአቸው፤ በእስራኤል ልጆች ሠራዊት መካከልም አገቡአቸው፤ እኒያ ከወዲያ፥ እኒህም ከወዲህ ሆነው አንድ እንኳን ሳይቀርና ሳያመልጥ ገደሉአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያደፈጡትም ሰዎች እንደዚሁ ከከተማዪቱ ወጥተው መጡባቸው። ስለዚህ እስራኤላውያን በዚያም በዚህም ስለ ከበቧቸው የጋይን ሰዎች ከመካከል አደረጓቸው፤ እስራኤላውያንም ሰዎቹን ፈጇቸው፤ አንድ እንኳ የተረፈ ወይም ያመለጠ አልነበረም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌሎቹም በእነርሱ ላይ ከከተማይቱ ወጡ፤ የጋይም ሰዎች በእስራኤል መካከል ሆኑ፥ እስራኤልም ከበቡአቸው፤ አንድ እንኳ ሳይቀር ሳያመልጥም ገደሉአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ከተማይቱም ገብተው የነበሩት እስራኤላውያን ወደ እነርሱ ወርደው የጦርነቱ ተካፋዮች ሆኑ፤ ስለዚህም የዐይን ሰዎች የተወሰኑ እስራኤላውያን በአንድ በኩል፥ ሌሎች ደግሞ በሌላ በኩል ከበዋቸው ስለ ነበረ ወደየትም ለማምለጥ አልቻሉም። ከእነርሱም አንድ እንኳ እንዳያመልጥ ወይም በሕይወት እንዳይኖር ሁሉንም ፈጁአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሌሎቹም በላያቸው ከከተማይቱ ወጡ፥ የጋይም ሰዎች በእስራኤል መካከል ሆኑ፥ እስራኤልም ከበቡአቸው፥ አንድ እንኳ ሳይቀር ሳያመልጥም ገደሉአቸው። |
አምላክህ እግዚአብሔርም በእጅህ አሳልፎ በሰጣቸውና በመታሃቸው ጊዜ፥ ፈጽመህ አጥፋቸው፤ ከእነርሱም ጋር ቃል ኪዳን አታድርግ፤ አትማራቸውም፤
በዚያም ቀን መቄዳን ያዟት፤ እርስዋንና ንጉሥዋንም በሰይፍ ስለት ገደሉ፤ በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ ፈጽመው አጠፉአቸው፤ ከእነርሱም አንዱን ስንኳ አላስቀሩም፤ የዳነም፥ ያመለጠም የለም፤ በኢያሪኮም ንጉሥ እንዳደረጉ በመቄዳ ንጉሥ አደረጉ።
ኢያሱም ከተማዋን፥ በከተማዪቱም ውስጥ የነበሩትን ሁሉ፥ ከወንድ እስከ ሴት፥ ከሕፃን እስከ ሽማግሌ፥ ከበሬ እስከ በግና እስከ አህያ በሰይፍ ስለት ፈጽሞ አጠፋ።
ኢያሱ፥ እስራኤልም ሁሉ ተደብቀው የነበሩት ከተማዪቱን እንደ ያዙ፥ የከተማዪቱም ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ ባዩ ጊዜ ወደኋላ ተመልሰው የጋይን ሰዎች ገደሉአቸው።