የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኢያሱ 21:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሌዊ ልጆች አለ​ቆች ወደ ካህኑ ወደ አል​ዓ​ዛር፥ ወደ ነዌም ልጅ ወደ ኢያሱ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ሕዝብ አባ​ቶች ነገ​ዶች አለ​ቆች መጡ፤

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የሌዋውያን ቤተ ሰብ አለቆች ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር፣ ወደ ነዌ ልጅ ወደ ኢያሱና ወደ ሌሎቹ የእስራኤል ነገድ አባቶች ዘንድ ቀረቡ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የሌዋውያን አባቶች አለቆች ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር፥ ወደ ነዌም ልጅ ወደ ኢያሱ፥ ወደ እስራኤልም ልጆች ነገዶች አለቆች ቀረቡ፤

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የሌዊ ነገድ ቤተሰቦች መሪዎች ወደ ካህኑ አልዓዛር፥ ወደ ነዌ ልጅ ኢያሱና ወደ እስራኤል ሕዝብ የነገድ መሪዎች ሄዱ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የሌዋውያን አባቶች አለቆች ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር፥ ወደ ነዌም ልጅ ወደ ኢያሱ፥ ወደ እስራኤልም ልጆች ነገዶች አለቆች ቀረቡ፥

ምዕራፉን ተመልከት



ኢያሱ 21:1
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቍጣ​ቸው ርጉም ይሁን፤ ጽኑ ነበ​ርና፤ ኵር​ፍ​ታ​ቸ​ውም ብርቱ ነበ​ርና፤ በያ​ዕ​ቆብ እከ​ፋ​ፍ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም እበ​ታ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ።


የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤት አለ​ቆች እነ​ዚህ ናቸው። የእ​ስ​ራ​ኤል የበ​ኵር ልጅ የሮ​ቤል ልጆች ሄኖኅ፥ ፍሉስ፥ አስ​ሮን፥ ከርሚ፤ እነ​ዚህ የሮ​ቤል ትው​ልድ ናቸው።


የአ​ሮ​ንም ልጅ አል​ዓ​ዛር ከፋ​ት​ኤል ልጆች ሚስ​ትን አገባ፤ እር​ስ​ዋም ፊን​ሐ​ስን ወለ​ደ​ች​ለት። እነ​ዚ​ህም በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው የሌ​ዋ​ው​ያን አባ​ቶች አለ​ቆች ናቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ በኢ​ያ​ሪኮ አን​ጻር በሞ​ዓብ ምዕ​ራብ እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ርስት ለሌ​ዋ​ው​ያን የም​ት​ሰ​ጡ​አ​ቸ​ውን ከተ​ሞች እን​ዲህ ስጡ፤ ከብ​ዙ​ዎቹ ብዙ፥ ከጥ​ቂ​ቶቹ ጥቂት ትወ​ስ​ዳ​ላ​ችሁ፤ እያ​ን​ዳ​ንዱ እንደ ወረ​ሱት እንደ ርስ​ታ​ቸው መጠን ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ለሌ​ዋ​ው​ያን ይሰ​ጣሉ።”


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በከ​ነ​ዓን ምድር የወ​ረ​ሱት ካህኑ አል​ዓ​ዛ​ርና የነዌ ልጅ ኢያሱ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ነገድ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው አለ​ቆች ያወ​ረ​ሱ​አ​ቸው ርስት ይህ ነው።


እነ​ር​ሱም ወደ ካህኑ ወደ አል​ዓ​ዛ​ርና ወደ ነዌ ልጅ ወደ ኢያሱ ወደ አለ​ቆ​ችም ቀር​በው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን መካ​ከል ርስት እን​ዲ​ሰ​ጠን በሙሴ እጅ አዘዘ” አሉ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ ከአ​ባ​ታ​ቸው ወን​ድ​ሞች ጋር ርስት ሰጣ​ቸው።


ካህኑ አል​ዓ​ዛር፥ የነ​ዌም ልጅ ኢያሱ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ነገ​ዶች የአ​ባ​ቶች አለ​ቆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በሴሎ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ አጠ​ገብ በዕጣ የተ​ካ​ፈ​ሉት ርስት ይህ ነው። ምድ​ሪ​ቱ​ንም መካ​ፈል ፈጸሙ።