Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 19:51 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

51 ካህኑ አል​ዓ​ዛር፥ የነ​ዌም ልጅ ኢያሱ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ነገ​ዶች የአ​ባ​ቶች አለ​ቆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በሴሎ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ አጠ​ገብ በዕጣ የተ​ካ​ፈ​ሉት ርስት ይህ ነው። ምድ​ሪ​ቱ​ንም መካ​ፈል ፈጸሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

51 እንግዲህ ካህኑ አልዓዛር፣ የነዌ ልጅ ኢያሱና የእስራኤል ነገድ የየጐሣ መሪዎች ሴሎ ላይ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ፣ በእግዚአብሔር ፊት ዕጣ ያደላደሉት ርስት ይህ ነው፤ የምድሪቱንም አከፋፈል በዚህ ሁኔታ ፈጸሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

51 ካህኑ አልዓዛር፥ የነዌም ልጅ ኢያሱ፥ የእስራኤልም ልጆች ነገዶች የአባቶች አለቆች በጌታ ፊት በሴሎ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በዕጣ ያከፋፈሉት ርስት ይህ ነው። ምድሪቱንም አከፋፍለው ጨረሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

51 ካህኑ አልዓዛር፥ የነዌ ልጅ ኢያሱና የእስራኤል ሕዝብ የነገድ አለቆች በሴሎ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ በእግዚአብሔር ፊት ለእስራኤል ሕዝብ በዕጣ ያከፋፈሉት ርስት ይህ ነው። በዚህም ዐይነት ምድሪቱን አከፋፍለው ጨረሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

51 ካህኑ አልዓዛር፥ የነዌም ልጅ ኢያሱ፥ የእስራኤልም ልጆች ነገዶች የአባቶች አለቆች በእግዚአብሔር ፊት በሴሎ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በዕጣ የተካፈሉት ርስት ይህ ነው። ምድሪቱንም መካፈል ጨረሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 19:51
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መን​ግ​ሥት ከይ​ሁዳ አይ​ጠ​ፋም፤ ምስ​ፍ​ናም ከአ​ብ​ራኩ፥ ለእ​ርሱ የሚ​ጠ​ብ​ቀ​ውን እስ​ኪ​ያ​ገኝ ድረስ፤ የአ​ሕ​ዛብ ተስ​ፋ​ቸው እርሱ ነውና፤


እርሱም “ጽዋዬንስ ትጠጣላችሁ፤ በቀኝና በግራ መቀመጥ ግን ከአባቴ ዘንድ ለተዘጋጀላቸው ነው እንጂ እኔ የምሰጥ አይደለሁም፤” አላቸው።


ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል ‘እናንተ የአባቴ ቡሩካን! ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።


ሥጋ በለ​በ​ሰው ሁሉ ላይ ሥል​ጣ​ንን እንደ ሰጠ​ኸው መጠን ለሰ​ጠ​ኸው ሁሉ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ።


ሰባ​ቱን የከ​ነ​ዓ​ንን አሕ​ዛብ አጥ​ፍቶ ምድ​ራ​ቸ​ውን አወ​ረ​ሳ​ቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በከ​ነ​ዓን ምድር የወ​ረ​ሱት ካህኑ አል​ዓ​ዛ​ርና የነዌ ልጅ ኢያሱ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ነገድ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው አለ​ቆች ያወ​ረ​ሱ​አ​ቸው ርስት ይህ ነው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በሴሎ ተሰ​በ​ሰቡ፤ በዚ​ያም የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ተከሉ፤ ምድ​ሩም ጸጥ ብሎ ተገ​ዛ​ላ​ቸው።


ኢያ​ሱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በሴሎ ዕጣ አጣ​ጣ​ላ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


እነ​ር​ሱም፥ “እነሆ፥ በቤ​ቴል በመ​ስዕ በኩል፥ ከቤ​ቴ​ልም ወደ ሰቂማ በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ በም​ሥ​ራቅ በኩል በሌ​ብና በዐ​ዜብ በኩል ባለ​ችው በሴሎ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓል በየ​ዓ​መቱ አለ” አሉ።


ተመ​ል​ከ​ቱም፤ እነሆ፥ የሴሎ ሴቶች ልጆች አታሞ ይዘው ለዘ​ፈን ሲወጡ ከወ​ይኑ ስፍራ ውጡ፤ ከሴሎ ሴቶች ልጆ​ችም ለየ​ራ​ሳ​ችሁ ሚስ​ትን ንጠቁ፤ ወደ ብን​ያም ምድ​ርም ሂዱ።


ያም ሰው በሴሎ ይሰ​ግድ ዘንድ፥ ለሠ​ራ​ዊት ጌታም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሠዋ ዘንድ ከከ​ተ​ማው ከአ​ር​ማ​ቴም በየ​ዓ​መቱ ይወጣ ነበር። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ካህ​ናት ሁለቱ የዔሊ ልጆች አፍ​ኒ​ንና ፊን​ሐስ በዚያ ነበሩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች