ያችም ሴት፥ “ለመግደል ባለ ደሞች እንዳይበዙ፤ ልጄንም እንዳይገድሉብኝ ንጉሥ ፈጣሪው እግዚአብሔርን ያስብ” አለች። እርሱም፥ “የልጅሽስ አንዲት የራሱ ጠጕር በምድር ላይ እንዳትወድቅ ሕያው እግዚአብሔርን” አላት።
ኢያሱ 20:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባለማወቅ ሳይወድድ ሰውን የገደለ በዚያ ይማፀን ዘንድ፥ ለእናንተ የመማፀኛ ከተሞችን ሥሩ፤ ነፍስ የገደለ ሰውም በአደባባይ ለፍርድ እስኪቀርብ ድረስ በደም ተበቃዩ አይገደል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳያስበው ድንገት ሰው የገደለ ማንኛውም ሰው ወደዚያ በመሸሽ ከደም ተበቃዩ እንዲያመልጥ ከተማዪቱ መጠለያ ትሁን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህም ከተሞች በስሕተት ሳያውቅም ሰውን የገደለ ገዳይ እንዲሸሽባቸው ከደም ተበቃዩ መማፀኛ ይሆኑላችኋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማንም ሰው ሳያውቅ በድንገት ሰው ቢገድል፥ ወደዚያ በመሄድ ሊበቀለው ከሚፈልገው ሰው ይድናል፤ |
ያችም ሴት፥ “ለመግደል ባለ ደሞች እንዳይበዙ፤ ልጄንም እንዳይገድሉብኝ ንጉሥ ፈጣሪው እግዚአብሔርን ያስብ” አለች። እርሱም፥ “የልጅሽስ አንዲት የራሱ ጠጕር በምድር ላይ እንዳትወድቅ ሕያው እግዚአብሔርን” አላት።
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ማናቸውም ሰው ሳያውቅ በእግዚአብሔር ፊት ኀጢአት ቢሠራ፥ እግዚአብሔርም፦ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዲቱን ቢተላለፍ፥
ነፍሰ ገዳዩ በማኅበሩ ፊት ለፍርድ እስከሚቆም ድረስ እንዳይሞት፥ ከተሞቹ ከደም ተበቃይ የመማፀኛ ከተሞች ይሁኑላችሁ።
የእግዚአብሔር ቃል ሐሰት ሊሆን አይቻልም፤ በእርሱ ለተማፀን ተጠብቆልን ባለ ተስፋችንም ማመንን ላጸናን ለእኛ ታላቅ ደስታ አለን።
ከእነዚህም ከተሞች በአንዲቱ ይማፀናል፤ በከተማዪቱም በር አደባባይ ቆሞ ለከተማዪቱ ሽማግሌዎች ነገሩን ይናገራል፤ እነርሱም ወደ ከተማዪቱ ያገቡታል። የሚቀመጥበትም ስፍራ ይሰጡታል።