“ወኅኒ ቤቱንም ዙሪያውን ተዘግቶ በቍልፍም ተቈልፎ አገኘነው፤ ወታደሮቹም በሩን ይጠብቁ ነበር፤ ነገር ግን ከፍተን በገባን ጊዜ በውስጥ ያገኘነው የለም” አሉአቸው።
ኢያሱ 2:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰዎቹም ወደ ዮርዳኖስ መሻገሪያ በሚወስደው መንገድ ተከተሉአቸው፤ በሩም ተቈለፈ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎቹም ሰላዮቹን በመከታተል ወደ ዮርዳኖስ መሻገሪያ የሚወስደውን መንገድ ይዘው ሄዱ፤ አሳዳጆቹ ወጥተው እንደ ሄዱም የቅጥሩ በር ተዘጋ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰዎቹም ወደ ዮርዳኖስ መሻገሪያ እስከሚወስደው መንገድ ድረስ አሳደዱአቸው፤ አሳዳጆችም ከወጡ በኋላ በሩ ተዘጋ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የንጉሡም መልእክተኞች ከከተማይቱ ወጥተው ሄዱ፤ የቅጽር በሩም ተዘጋ፤ መልእክተኞቹም ሰላዮችን በመፈለግ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግሮ እስከሚያልፈው ስፍራ ድረስ ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰዎቹም ወደ ዮርዳኖስ መሻገሪያ በሚወስደው መንገድ አሳደዱአቸው፥ አሳዳጆችም ከወጡ በኋላ በሩ ተቈለፈ። |
“ወኅኒ ቤቱንም ዙሪያውን ተዘግቶ በቍልፍም ተቈልፎ አገኘነው፤ ወታደሮቹም በሩን ይጠብቁ ነበር፤ ነገር ግን ከፍተን በገባን ጊዜ በውስጥ ያገኘነው የለም” አሉአቸው።
በሩም ሲዘጋ፥ ሲጨልምም ሰዎቹ ወጡ፤ ወዴት እንደ ሄዱ አላውቅም፤ ፈጥናችሁ ተከተሉአቸው፤ ምንአልባት ታገኙአቸው ይሆናል” አለቻቸው።
የገለዓድ ሰዎችም ኤፍሬም በሚያልፍበት በዮርዳኖስ ማዶ ደረሱባቸው። ከዚህ በኋላ ከኤፍሬም ያመለጡት እንሻገር ባሉ ጊዜ የገለዓድ ሰዎች፥ “በውኑ እናንተ ከኤፍሬም ወገን ናችሁን?” ቢሉአቸው “አይደለንም” አሉ።
እርሱም፥ “እግዚአብሔር አምላክ ጠላቶቻችንን ሞዓባውያንን በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶናልና ተከተሉኝ” አላቸው። ተከትለውትም ወረዱ፤ ወደ ሞዓብም የሚያሻግረውን የዮርዳኖስን መሻገርያ ያዙ፤ ማንም ሰው እንዲያልፍ አልፈቀዱም።