የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኢያሱ 2:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በሩም ሲዘጋ፥ ሲጨ​ል​ምም ሰዎቹ ወጡ፤ ወዴት እንደ ሄዱ አላ​ው​ቅም፤ ፈጥ​ና​ችሁ ተከ​ተ​ሉ​አ​ቸው፤ ምን​አ​ል​ባት ታገ​ኙ​አ​ቸው ይሆ​ናል” አለ​ቻ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ጨልሞ የቅጥሩ በር ከመዘጋቱ በፊት ወጥተው ሄደዋል፤ በየት በኩል እንደ ሄዱ ግን እኔ አላውቅም፤ ልትደርሱባቸው ትችላላችሁና ፈጥናችሁ ተከታተሏቸው።”

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በሩ በሚዘጋበት ጊዜ ሲመሻሽ ሰዎቹ ወጥተው ሄደዋል፤ ወዴት እንደ ሄዱ ግን አላውቅም፤ ፈጥናችሁ አሳድዱአቸው፥ ትደርሱባቸዋላችሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ጊዜው መሽቶ በመጨለሙ በሩ ሲዘጋ ሰዎቹ ወጥተው ሄዱ፤ ወዴት እንደ ሄዱ ግን አላውቅም፤ ፈጥናችሁ ብታሳድዱአቸው ትደርሱባቸዋላችሁ” አለች።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በሩም ሲዘጋ ሲጨልምም ሰዎቹ ወጡ፥ ወዴት እንደ ሄዱ አላውቅም፥ ፈጥናችሁ አሳድዱአቸው፥ ታገኙአቸውማላችሁ አለች።

ምዕራፉን ተመልከት



ኢያሱ 2:5
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚህ በኋላ ሰን​በት ከመ​ግ​ባቱ በፊት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሮች ድን​ግ​ዝ​ግ​ዝታ በሆነ ጊዜ በሮ​ችዋ እን​ዲ​ዘጉ፥ ሰን​በ​ትም እስ​ኪ​ያ​ልፍ ድረስ እን​ዳ​ይ​ከ​ፈቱ አዘ​ዝሁ። በሰ​ን​በ​ትም ቀን ሸክም እን​ዳ​ይ​ገባ ከብ​ላ​ቴ​ኖች በዐ​ያ​ሌ​ዎቹ በሮ​ች​ዋን አስ​ጠ​በ​ቅሁ።


በሮ​ች​ሽም ሁል​ጊዜ ይከ​ፈ​ታሉ፤ ሰዎች የአ​ሕ​ዛ​ብን ብል​ጽ​ግና፥ የተ​ማ​ረ​ኩ​ት​ንም ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ወደ አንቺ ያመጡ ዘንድ ሌሊ​ትና ቀን አይ​ዘ​ጉም።


በዚያ ወራት በዚ​ያም ዘመን፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እነ​ዚ​ህን በም​ድር የተ​ረ​ፉ​ትን ይቅር እላ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና የእ​ስ​ራ​ኤል በደል ይፈ​ለ​ጋል፤ አይ​ኖ​ር​ምም፤ የይ​ሁ​ዳም ኀጢ​አት ይፈ​ለ​ጋል፥ ምንም አይ​ገ​ኝም።


በወ​ን​ዙም አጠ​ገብ በዳሩ ላይ በዚ​ህና በዚያ ፍሬው የሚ​በላ ዛፍ ሁሉ ይበ​ቅ​ላል፤ ቅጠ​ሉም አይ​ረ​ግ​ፍም፤ ፍሬ​ውም አይ​ጐ​ድ​ልም፤ ውኃ​ውም ከመ​ቅ​ደስ ይወ​ጣ​ልና በየ​ወሩ ሁሉ የፍሬ በኵር ያገ​ኛል፤ ፍሬ​ውም ለመ​ብል፥ ቅጠ​ሉም ለመ​ድ​ኀ​ኒት ይሆ​ናል።”


ሴቲ​ቱም ሁለ​ቱን ሰዎች ወስዳ ሸሸ​ገ​ቻ​ቸው፤ እር​ስ​ዋም፥ “አዎን፥ ሰዎቹ ወደ እኔ መጡ፤ ከወ​ዴት እንደ ሆኑ ግን አላ​ወ​ቅ​ሁም፤


እር​ስዋ ግን ወደ ሰገ​ነቱ አው​ጥታ በተ​ከ​መረ እን​ጨት መካ​ከል በቀ​ር​ከሃ ጠቅ​ልላ ደብ​ቃ​ቸው ነበር።


ሰዎ​ቹም ወደ ዮር​ዳ​ኖስ መሻ​ገ​ሪያ በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ ተከ​ተ​ሉ​አ​ቸው፤ በሩም ተቈ​ለፈ።


በዚያም ሌሊት ስለሌለ ደጆችዋ በቀን ከቶ አይዘጉም፤


ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን ይዘው እን​ዲ​ያ​መ​ጡት መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እር​ስ​ዋም ታሞ​አል አለ​ቻ​ቸው።