ወልደ አዴርም ለንጉሡ ለአሳ እሺ አለው፤ የሠራዊቱንም አለቆች በእስራኤል ከተሞች ላይ ሰድዶ ኢናንንና ዳንን፥ አቤልቤትመዓካንና ኬኔሬትን ሁሉ የንፍታሌምንም ሀገር ሁሉ መታ።
ኢያሱ 19:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የንፍታሌም ልጆች ነገድ ርስት እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ ለንፍታሌም ነገድ ርስት ሆነው በየጐሣው የተደለደሉ ከተሞችና መንደሮች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የንፍታሌም ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እነዚህ ታላላቅና ታናናሽ ከተሞች ለንፍታሌም ነገድ በየወገናቸው ርስት ሆኖ በተሰጠው ምድር ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የንፍታሌም ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው። |
ወልደ አዴርም ለንጉሡ ለአሳ እሺ አለው፤ የሠራዊቱንም አለቆች በእስራኤል ከተሞች ላይ ሰድዶ ኢናንንና ዳንን፥ አቤልቤትመዓካንና ኬኔሬትን ሁሉ የንፍታሌምንም ሀገር ሁሉ መታ።