ኢያሱ 18:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም የእስራኤልን ልጆች አላቸው፥ “የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ምድር እንዳትወርሱአት እስከ መቼ ድረስ ታቈዩአታላችሁ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ኢያሱ እስራኤላውያንን እንዲህ አላቸው፤ “የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ምድር ለመውረስ ቸል የምትሉት እስከ መቼ ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱም የእስራኤልን ልጆች እንዲህ አላቸው፦ “የአባቶቻችሁ አምላክ ጌታ የሰጣችሁን ምድር ገብታችሁ ለመውረስ እስከ መቼ ቸል ትላላችሁ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ኢያሱ ለእስራኤላውያን እንዲህ አለ፦ “ገብታችሁ የቀድሞ አባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ምድር ሳትወርሱ የምትቈዩት እስከ መቼ ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱም የእስራኤልን ልጆች አላቸው፦ የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ምድር ትወርሱ ዘንድ እስከ መቼ ለመግባት ቸል ትላላችሁ? |
አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና ዐሳብ፥ ዕውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምትችለውን ሁሉ እንደ ኀይልህ አድርግ።
የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ለዘለዓለም ሕይወት ለሚኖር መብል ሥሩ እንጂ ለሚጠፋው መብል አይደለም፤ ይህን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና።”
ኢያሱም ሸመገለ፤ ዘመኑም አለፈ፤ እግዚአብሔርም ኢያሱን አለው፥ “እነሆ ዘመንህ አለፈ፤ ያልተወረሰች እጅግ ብዙ ምድር ገና ቀርታለች፤
ከየነገዳችሁ ሁሉ ሦስት ሦስት ሰዎችን አምጡ፥ ተነሥተውም ሀገሪቱን ይዙሩአት፤ ለመክፈልም እንዲያመች ገልጠው ይጻፉአት፤ ወደ እኔም ይመለሳሉ።
እነርሱም፥ “ምድሪቱ እጅግ መልካም እንደ ሆነች አይተናል፤ ተነሡ፤ በእነርሱ ላይ እንውጣ፤ እናንተ ዝም ትላላችሁን? ትሄዱ ዘንድ፥ ምድሪቱንም ለመውረስ ትገቡ ዘንድ ቸል አትበሉ።