ከዚያም ድንበራቸው ወደ ቤተ ገለዓም ይወጣል፤ በቤትዓረባ በሰሜን በኩል ያልፋል፤ ድንበራቸውም ወደ ሮቤል ልጅ ወደ ሊቶን ቢዮን ይወጣል፤
ኢያሱ 18:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰሜንም በኩል ወደ ቤተ ራባ ጀርባ ያልፋል። በመስዕም ወደ ባሕር መንገድ ይወርዳል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ቤትዓረባ ሰሜናዊ ተረተር በመቀጠል ቍልቍል ወደ ዓረባ ይወርዳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰሜንም ወገን ወደ ዓረባ አጠገብ አለፈ፥ ወደ ዓረባም ወረደ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በስተሰሜን በኩል በዮርዳኖስ ሸለቆ ትይዩ በሚገኘው ተረተር በኩል አልፎ ይወርዳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሰሜንም ወገን ወደ ዓረባ አጠገብ አለፈ፥ ወደ ዓረባም ወረደ፥ |
ከዚያም ድንበራቸው ወደ ቤተ ገለዓም ይወጣል፤ በቤትዓረባ በሰሜን በኩል ያልፋል፤ ድንበራቸውም ወደ ሮቤል ልጅ ወደ ሊቶን ቢዮን ይወጣል፤
ወደ ቤተሳሚስም ምንጭ ያልፋል፤ በኢታሚም አቀበት ፊት ለፊት ወዳለው ወደ ኬልዩት ይገባል፤ ወደ ሮቤልም ልጅ ወደ ቤዎን ድንጋይ ይወርዳል፤
የድንበራቸውም ፍጻሜ በሰሜን በኩል ወደ ጨው ባሕር ልሳን ይደርሳል፤ በደቡብም በኩል ድንበራቸው ዮርዳኖስ ነው። ይህም በደቡብ በኩል ያለው ድንበር ነው።