አባቱም እንቢ አለ፤ እንዲህ ሲል፥ “አውቃለሁ ልጄ ሆይ፥ አውቃለሁ፤ ይህም ደግሞ ሕዝብ ይሆናል፤ ታላቅም ይሆናል፤ ነገር ግን ታናሽ ወንድሙ ከእርሱ ይበልጣል፤ ዘሩም ብዙ ሕዝብ ይሆናል።”
ኢያሱ 17:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዮሴፍም ልጆች ኢያሱን፥ “እኛ ብዙ ሕዝብ ስንሆን እስከ አሁንም እግዚአብሔር ስለ ባረከን ለምን አንድ ክፍል፥ አንድም ዕጣ ብቻ ርስት አድርገህ ሰጠኸን?” ብለው ወቀሱት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዮሴፍ ዘሮች ኢያሱን፣ “ቍጥራችን ብዙ ነው፤ እግዚአብሔርም አብዝቶ ባርኮናል፤ ታዲያ እንዴት ርስታችን አንድ ዕጣና አንድ ድርሻ ብቻ ሆነ?” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዮሴፍ ልጆች ነገድ ኢያሱን እንዲህ አለው፦ “እኔ ብዙ ሕዝብ ስለ ሆንኩ እስከ አሁንም ጌታ ስለ ባረከኝ ለምን አንድ ድርሻ አንድም ዕጣ ብቻ ርስት አድርገህ ሰጠኸኝ?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዮሴፍ ነገድ ወደ ኢያሱ ቀርበው “እግዚአብሔር ባርኮን ለበዛነው ለእኛ እንዴት አንድ ዕጣ ብቻ ሰጠኸን?” ብለው ጠየቁት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዮሴፍ ልጆች ኢያሱን፦ እኔ ብዙ ሕዝብ ስለ ሆንሁ እስከ አሁንም እግዚአብሔር ስለ ባረከኝ ለምን አንድ ክፍል አንድም ዕጣ ብቻ ርስት አድርገህ ሰጠኸኝ? አሉት። |
አባቱም እንቢ አለ፤ እንዲህ ሲል፥ “አውቃለሁ ልጄ ሆይ፥ አውቃለሁ፤ ይህም ደግሞ ሕዝብ ይሆናል፤ ታላቅም ይሆናል፤ ነገር ግን ታናሽ ወንድሙ ከእርሱ ይበልጣል፤ ዘሩም ብዙ ሕዝብ ይሆናል።”
በዚያም ቀን እንዲህ ብሎ ባረካቸው፥ “በእናንተ እስራኤል እንዲህ ተብሎ ይባረካል፦ እግዚአብሔር እንደ ኤፍሬምና እንደ ምናሴ ይባርክህ።” ኤፍሬምንም ከምናሴ ፊት አደረገው።
እኔም ከአሞራውያን እጅ በሰይፌና በቀስቴ የወሰድሁትን ምርኮ ለአንተ ከወንድሞችህ የተሻለውን እሰጥሃለሁ” አለው።
ለብዙዎቹ ብዙ ርስትን ትሰጣቸዋለህ፤ ለጥቂቶችም ጥቂት ርስትን ትሰጣቸዋለህ። ለእያንዳንዳቸው እንደ ቍጥራቸው መጠን ርስታቸውን ትሰጣቸዋለህ።
ኢያሱም፥ “ብዙ ሕዝብ ከሆናችሁ፥ ተራራማው የኤፍሬም ሀገርም ከጠበባችሁ ወደ ዱር ወጥታችሁ መንጥራችሁ አቅኑአት” አላቸው።