በይሳኮርና በአሴር መካከል ቤትሳንና መንደሮችዋ፥ ዶርና መንደሮችዋ፥ መጌዶና መንደሮችዋ፥ የመፌታ ሦስተኛ እጅና መንደሮችዋ ለምናሴ ነበሩ።
ኢያሱ 17:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በደቡብ በኩል ያለው ለኤፍሬም ነበረ፤ በሰሜን በኩል ያለውም ለምናሴ ነበረ፤ ድንበሩም ባሕር ነበረ፤ በሰሜን በኩል ወደ አሴር፥ በምሥራቅም በኩል ወደ ይሳኮር ይደርሳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በደቡብ በኩል ያለው ምድር የኤፍሬም ሲሆን፣ በሰሜን በኩል ያለው ደግሞ የምናሴ ነበር፤ የምናሴ ግዛት እስከ ባሕሩ የሚደርስ ሲሆን፣ ሰሜናዊ ድንበሩ አሴር፣ ምሥራቃዊ ድንበሩ ደግሞ ይሳኮር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በደቡብ በኩል ያለው ለኤፍሬም ነበረ፥ በሰሜንም በኩል ያለው ለምናሴ ነበረ፥ ድንበሩም የባሕሩ ዳርቻ ነበረ፤ በሰሜን በኩል ወደ አሴር፥ በምሥራቅም በኩል ወደ ይሳኮር ደረሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም የተነሣ የሁለቱም ምዕራባዊ ወሰን የሜድትራኒያን ባሕር ሆኖ ኤፍሬም በደቡብ፥ ምናሴ በሰሜን እንዲሰፍሩ ተደረገ፤ አሴር በሰሜን ይሳኮር ደግሞ በምሥራቅ ሰፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በደቡብ በኩል ያለው ለኤፍሬም ነበረ፥ በሰሜንም በኩል ያለው ለምናሴ ነበረ፥ ድንበሩም ባሕሩ ነበረ፥ በሰሜን በኩል ወደ አሴር፥ በምሥራቅም በኩል ወደ ይሳኮር ደረሰ። |
በይሳኮርና በአሴር መካከል ቤትሳንና መንደሮችዋ፥ ዶርና መንደሮችዋ፥ መጌዶና መንደሮችዋ፥ የመፌታ ሦስተኛ እጅና መንደሮችዋ ለምናሴ ነበሩ።
ድንበራቸውም በደቡብ በኩል ወዳለው ወደ ቃራና ሸለቆና ወደ ኢያሪያል ሸለቆ ይወርዳል፤ የኤፍሬም ዕጣ የሆነው ጤሬሜንቶስ የሚባለው ዛፍም በምናሴ ከተሞች መካከል አለ፤ የምናሴም ድንበር በሰሜን በኩል ወደ ወንዙ ይወርዳል፤ መውጫውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ።