የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኢያሱ 16:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ይኸ​ውም በም​ናሴ ልጆች ርስት መካ​ከል ለኤ​ፍ​ሬም ልጆች ከተ​ለዩ ከተ​ሞች ጋር፥ ከተ​ሞች ሁሉ ከመ​ን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው ጋር ነው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይህም በምናሴ ነገድ ርስት ውስጥ ለኤፍሬም ዘሮች የተመደቡትን ከተሞች በሙሉና መንደሮቻቸውን የሚያጠቃልል ነው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ይኸውም በምናሴ ልጆች ርስት መካከል ለኤፍሬም ልጆች ከተለዩ ከተሞች ጋር፥ እነዚህም ከተሞች ሁሉ ከመንደሮቻቸው ጋር ርስታቸው ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እርሱም በምናሴ ርስት ክልል ውስጥ ያሉትንና ለኤፍሬማውያን የተሰጡትን ከተሞችና መንደሮችንም ይጨምራል፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ይኸውም በምናሴ ልጆች ርስት መካከል ለኤፍሬም ልጆች ከተለዩ ከተሞች ጋር፥ ከተሞች ሁሉ ከመንደሮቻቸው ጋር፥ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት



ኢያሱ 16:9
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በገ​ለ​ዓ​ድና በታ​ሲሪ፥ በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ልም፥ በኤ​ፍ​ሬ​ምም፥ በብ​ን​ያ​ምም፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ላይ አነ​ገ​ሠው።


ግዛ​ታ​ቸ​ውና ማደ​ሪ​ያ​ቸው ቤቴ​ልና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ነዓ​ራን፥ በም​ዕ​ራ​ብም በኩል ጌዝ​ርና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ ደግ​ሞም ሴኬ​ምና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ እስከ ጋዛና እስከ መን​ደ​ሮ​ችዋ ድረስ፤


ከም​ና​ሴም ድን​በር ቀጥሎ ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ለኤ​ፍ​ሬም አንድ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል።


በጋ​ዜ​ርም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንን ኤፍ​ሬም አላ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም፤ እስከ ዛሬም ድረስ ከነ​ዓ​ና​ው​ያን በኤ​ፍ​ሬም መካ​ከል ተቀ​ም​ጠ​ዋል፤ ገባ​ርም ሆኑ።


ድን​በ​ሩም ከጣፉ ወደ ባሕር እስከ ኬል​ቃን ወንዝ ድረስ ያል​ፋል፥ መው​ጫ​ውም በባ​ሕሩ አጠ​ገብ ነበረ። የኤ​ፍ​ሬም ልጆች ነገድ ርስት በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ይህ ነበረ።


ድን​በ​ራ​ቸ​ውም በደ​ቡብ በኩል ወዳ​ለው ወደ ቃራና ሸለ​ቆና ወደ ኢያ​ሪ​ያል ሸለቆ ይወ​ር​ዳል፤ የኤ​ፍ​ሬም ዕጣ የሆ​ነው ጤሬ​ሜ​ን​ቶስ የሚ​ባ​ለው ዛፍም በም​ናሴ ከተ​ሞች መካ​ከል አለ፤ የም​ና​ሴም ድን​በር በሰ​ሜን በኩል ወደ ወንዙ ይወ​ር​ዳል፤ መው​ጫ​ውም በባ​ሕሩ አጠ​ገብ ነበረ።