የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኢያሱ 1:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“አገ​ል​ጋዬ ሙሴ ሞቶ​አል፤ አሁ​ንም አን​ተና ይህ ሕዝብ ሁሉ ተነ​ሥ​ታ​ችሁ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወደ​ም​ሰ​ጣ​ቸው ምድር ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገሩ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“እነሆ፤ ባሪያዬ ሙሴ ሞቷል፤ እንግዲህ አሁንም አንተና ይህ ሕዝብ ሁሉ ተነሡ፤ ለእስራኤላውያን ወደምሰጣቸው ምድር ለመግባት የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻገሩ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“ባርያዬ ሙሴ ሞቷል፤ እንግዲህ አሁን አንተና ይህ ሕዝብ ሁሉ ተነሥታችሁ ለእስራኤል ልጆች ወደምሰጣቸው ምድር ይህን ዮርዳኖስ ተሻገሩ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“እነሆ! አገልጋዬ ሙሴ ሞቶአል፤ እንግዲህ አንተና የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ እኔ ለእናንተ ለእስራኤል ልጆች ወደማወርሳት ምድር ለመግባት የዮርዳኖስን ወንዝ ለመሻገር ተዘጋጁ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ባሪያዬ ሙሴ ሞቶአል፥ አሁንም አንተና ይህ ሕዝብ ሁሉ ተነሥታችሁ ለእስራኤል ልጆች ወደምሰጣቸው ምድር ይህን ዮርዳኖስ ተሻገሩ።

ምዕራፉን ተመልከት



ኢያሱ 1:2
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በው​ስ​ጥዋ የም​ት​ኖ​ር​ባ​ትን ይህ​ችን ምድር፥ የከ​ነ​ዓ​ንን ምድር ሁሉ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይገ​ዙ​አት ዘንድ ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ለሁ፤ አም​ላ​ክም እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ።”


ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት አበ​ዛህ፤ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ወደ ተና​ገ​ር​ህ​ላ​ቸው ምድር አገ​ባ​ሃ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰይ​ጣ​ንን አለው፥ “በባ​ሪ​ያዬ በኢ​ዮብ ላይ የም​ታ​ስ​በው ነገር እን​ዳ​ይ​ኖር ተጠ​ን​ቀቅ! በም​ድር ላይ እንደ እርሱ ቅን፥ ንጹ​ሕና ጻድቅ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የሚ​ፈራ፥ ከክፉ ሥራም ሁሉ የራቀ ሰው የለ​ምና።”


እነሆ፥ ደግፌ የያ​ዝ​ሁት ባሪ​ያዬ ያዕ​ቆብ፤ ነፍሴ የተ​ቀ​በ​ለ​ችው ምርጤ እስ​ራ​ኤ​ልም፤ በእ​ርሱ ላይ መን​ፈ​ሴን አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ እር​ሱም ለአ​ሕ​ዛብ ፍር​ድን ያመ​ጣል።


አገ​ል​ጋዬ ሙሴ ግን እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ እርሱ በቤቴ ሁሉ የታ​መነ ነው።


ኢያሱ በዚህ ሕዝብ ፊት ይሻ​ገ​ራ​ልና፥ አን​ተም የም​ታ​ያ​ትን ምድር እርሱ ያወ​ር​ሳ​ቸ​ዋ​ልና ኢያ​ሱን እዘ​ዘው፤ አደ​ፋ​ፍ​ረ​ውም፥ አጽ​ና​ውም።


ሙሴም ኢያ​ሱን ጠርቶ በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ፊት፦ ‘አንተ ከዚህ ሕዝብ ጋር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው እን​ዲ​ሰጥ ወደ ማለ​ላ​ቸው ምድር ትገ​ባ​ለ​ህና፥ እር​ስ​ዋ​ንም ለእ​ነ​ርሱ ታወ​ር​ሳ​ለ​ህና ጽና፤ በርታ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በዚያ በሞ​ዓብ ምድር ሞተ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ ከሞተ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሙ​ሴን አገ​ል​ጋይ የነ​ዌን ልጅ ኢያ​ሱን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


“በሰ​ፈሩ መካ​ከል ዕለፉ፥ ሕዝ​ቡ​ንም፦ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት አድ​ርጎ ወደ​ሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር እስከ ሦስት ቀን ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ግ​ራ​ችሁ ልት​ወ​ር​ሱ​አት ትገ​ቡ​ባ​ታ​ላ​ች​ሁና ስን​ቃ​ች​ሁን አዘ​ጋጁ ብላ​ችሁ እዘ​ዙ​አ​ቸው።”